የግንባታ ማቴሪያል ግዥ - 10,000 ሊትር ሮቶ /ውሃ ማጠራቀሚያ/
የግንባታ ማቴሪያል ግዥ
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በጽ/ቤቱ ሥር ለሚገኙ ለቄራ አገልግሎት ስራ ሱፐር ፋይበር 10,000 ሊትር ሮቶ /ውሃ ማጠራቀሚያ/እቃ ግዥ ለመፈፀም በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት ፡- 1 የግንባታ ማቴሪያል እቃ ግዥ
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆኑ: -
1. ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ፤ ለስራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/tin/ ያላቸው፣ ግዥው ከ200,000 ብር በላይ የሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለበት።
2. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 33 በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮ. ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኤንቨሎፖች በአብክመ የከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዢ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው /16/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ 10,000 ሊትር ሮቶ የውሃ ማጠራቀሚያ ግዥ ጨረታ ሰነድ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው 25/12/18 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት 10,000 ሊትር ሮቶ የውሃ ማጠራቀሚያ እቃዎች ግዥ ላይ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ሎት 1 -- 10,000 /አስር ሺህ ብር/
6. የግንባታ ማቴሪያል እቃ ግዥ የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ፤ በከሚሴ ከተማ እና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር 033 554 0255 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
በከሚሴ ከ/አስ/ የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
