Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 6 18 61 25
  • Website
  • Deadline20 Aug 2018, 8:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) (non-refundable)
  • opening date2018-08-20 08:30
  • Categories Agriculture And Farming , Sales, Disposals And Foreclosure , Agricultural Products

የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል ሽያጭ


የጨረታ ማስታወቂያ

የምግብ እህልና የብጣሪ እህል ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ኢግስኮ-ምዘአዘ/ጨሽ/ 01ሠነድ/2018

 

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ በአርዳይታ፣ በኮፈሌ፣ በሀዋሳ፣ ቦንጋ፤ ነቀምት፣ ባህርዳር፣ ቻግኒ እና አሰላ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ላይ የሚገኘውን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ስለሚፈልግ፡-

1.      ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ።

2.    ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ (Seed Forest products Supply Sector) ስም የጨረታ ማስከበሪያ (Bid BOND) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም የባንክ ጋራንቲ ዋስትና ማስያዝ አለበት።

3.    ማንናውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሱት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ወይም ከአዲስ አበባ ዋናው መ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

4.    ማንኛውም ተጫራች የተገለፀውን መጠን የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል መጫረት ይችላል፤

5.    ማንኛውም ተጫራች የምግብ እህሉ እና የብጣሪ እህሉ በሚገኙበት ቅ/ጽ/ቤቶች በመገኘት አይቶ መጫረት አለበት። ይህን ሳያደርግ ዋጋ ቢያቀርብ ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።

6.    ማንኛውምተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚጠይቀውን በሙሉ አሟልቶ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

7.    ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

8.    የምግብ እህልና የብጣሪ እህል መጠን በዚህ ጨረታ ሰነድ ላይ ከተገለፀው መጠን ሊያንስ ይችላል።

9.    ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የምግብ እህል እና የብጣሪ እህል ዓይነት የሚሰጠውን ዋጋ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለበት። ጨረታው ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ሰዓት ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዘርፉ ጽ/ቤት እና ከላይ በተጠቀሱት ቅ/ጽ/ ቤቶች ጨረታው ይከፈታል።

10.   መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፦ 09-11-31-35-79

አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ምርጥ ዘር አቅርቦት ዘርፍ

✨ messages.ai_summary
Sale of food grains and malting barley by the Ethiopian Agricultural Works Corporation's Seed Supply Sector via open tender. Bidders must hold a renewed trade license and pay current taxes. Grains are located at branch offices in Ardayita, Kofele, Hawassa, Bonga, Nekemte, Bahir Dar, Chagni, and Asella.
Save Tender