Motorcycle Purchase
የጨረታ ማስታወቂያ
ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም በ2018 ዓ.ም ሞተር ሣይከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ ቀጥሎ ያሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች፡-
1. በዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ቫት የተመዘገቡበት ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
2. ከፋይናንስና ኢ/ል/ቢሮ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋገጥ የምዝገባ ሰርተፊኬት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Security) ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ብር 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ CPO ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታው ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ለዶክመንት የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብቻ በመክፈል ከማርጯ/አ/የፋ/ተቋም ፋይናንስ መምሪያ ድረስ በመቅረብ ወይም በኢት/ያ ንግድ ባንክ ማርጪ አነስተኛ ፋይናንስ ተቋም ስም በተከፈተው ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000564691252 ገንዘብ ገቢ በማድረግ ያስገቡበትን የባንክ አድቫይሱን በE-mail: marchuwa23@gmail.com በመላክ በስልክ ቁጥር 0949616937 ደውለው በመግለጽ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጋዜጣው ከወጣበት አሥር /10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ስለሆነ ተጫራቾች ወላይታ ሶዶ ወልማ ህንጻ ላይ ቢሮ ቁጥር 1 መ/ቤቱ ለዚሁ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ሣጥን ጋዜጣ ከወጣበት አሥር/10/ ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ4፡15 ሰዓት በቢሮ ይከፈታል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046-180-76-66
ማርጯ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም
