በልስቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግል ማህበር አዲስ አበባ ታጠቅ ግቢ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም የተሸከርካሪና ማሽነሪ ጎማዎችን፣ቁርጥራጭ ብረቶች፣የተቃጠለ ዘይት፣ባትሪዎች፣እና እንጨቶች…ወዘተ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ የተለያዩ ዓይነት ንብረቶች ሽያጭ የወጣ ማስታወቂያ
በልስቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/ የግል ማህበር አዲስ አበባ ታጠቅ ግቢ የሚገኙ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም የተሸከርካሪና ማሽነሪ ጎማዎችን፣ቁርጥራጭ ብረቶች፣የተቃጠለ ዘይት፣ባትሪዎች፣እና እንጨቶች…ወዘተ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች የቀረቡትን መስፈርቶች የምታሟሉ ጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ይጋብዛል::
- ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው::
- የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታው ጠቅላላ ዋጋ 5% በC.P.O ማስያዝ አለባቸው::
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ውል ማስከበሪያ (Performance Guaranty) ያሸነፈውን ዋጋ 5% በC.P.O ማስያዝ አለበት::
- ተጫራጮች እያንዳንዱ ለሽያጭ የቀረበ ንብረት ዋጋ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው::
- የቀረበው ዋጋ 15% (ቫት) ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታው ላይ የተዘረዘሩትን ንብረት ካሸነፈበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ሳምንት ውስጥ በራሳቸው ማጓጓዣ ከበልስቲ ትሬዲንግ ግቢ ማንሳት አለባቸው::ማንሳት ካልቻሉ ቀደም ብሎ ያስያዙትን ውል ማስከበሪያ (Performance Guaranty) ብር ገቢ ተደርጎ ለሁለተኛ አሸናፊ ይሰጣል (ጨረታው ይሰረዛል)::
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ በታሸገ ኢንቬሎፕ ቦሌ(ማተሚያ ጀርባ) በሚገኘው ኢትዮ-ቤስት ሪልእስቴት ታወር 5ተኛ ፎቅ በተዘጋጀ ሳጥን ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም ጠዋት 3:30 ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ10ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን ማወቅ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚፈልጉት ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111561805 ወይም 0944308793 በስራ ሰዓት በመደወል ማግኘት ይችላሉ::
- ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
በልስቲ ትሬዲንግ ኃላ/የተ/ የግል ማህበር
