በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለገላን ወረዳ ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚውል ኮድ 3 የሆነ እና ደብል ካፕ ወይም አነስተኛ መኪኖችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ገ/ወ/ገ/ጽ/ቤት 001/2019
በሸገር ከተማ በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለገላን ወረዳ ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ ትራንስፖርት አገልግልግሎት የሚውል ኮድ 3 የሆነ እና ደብል ካፕ ወይም አነስተኛ መኪኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የግብር መለያ ቁጥር እና የመንግስት ግብር ለመክፈላቸው ከገቢዎች ቢሮ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዘጋቢ የሆኑ እና እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ለ15/ለአስራ አምስት /የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ /በገላን ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ሲንቄ ባንክ ቁጥር 1064793701213 የጨረታውን ሰነድ ከገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይህ ማሳታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው /አስራ ስድስተኛው/ የስራ ቀናት በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነዱን በመሙላትና ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ከረፋዱ እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡30 በገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚውል በባንክ በተረጋገጠ CPO 10,000/አስር ሺህ/ ብር ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
8. ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ዝርዝር መሰረት ሞልተው መመለስ ይኖርባቸዋል።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦ 0913 321 839 / 0910 742 350 / 0911 827 152
በገላን ክፍለ ከተማ የገላን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
