በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አገልግሎት ለሚሰጣቸው የወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት አመት ለሴክተር መስሪያ ቤቶች የመኪና መለዋወጫ እቃዎችና የመኪና ጎማዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም፤
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፣
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ኦሪጂናል ዕቃ መሙላት እና ያሸነፉባቸውን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ከግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 15% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያስይዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦሪጂናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዝ ይሆናል።
- ውድድሩ የሚካሄደው በጠቅላላ በሎት ድምር ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል። የመከፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0912716922 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
- በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ
አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች/ ኦሪጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም በየፑሉ በሚገኘው ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
በደቡብ ወሎ ዞን የአርጎባ ብሄረሰብ ልዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of vehicle spare parts and tires for sector offices in the Argoba special district, South Wollo Zone, via open national tender. Bidders need a valid trade license, TIN, and VAT registration if applicable. Winners must supply original goods and undergo inspection.
