በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎች ዶዘር፣ ኤሰክቨቴር፣ ግሬድር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ደምፕ ትራክ፣ ሸዋር ትራከ፣ ሎቤድ እና የተለያዩ የፒካፕ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡001/2019
በሸገር ከተማ የመልካ ኖኖ ክ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የመንገድ ሥራ ማሽነሪዎች ዶዘር፣ ኤሰክቨቴር፣ ግሬድር፣ ሎደር፣ ሮለር፣ ደምፕ ትራክ፣ ሸዋር ትራከ፣ ሎቤድ እና የተለያዩ የፒካፕ መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው የተጫራቾች መመሪያ መሠረት ጨረታውን እንድትካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የጨረታ ዝርዝር ሁኔታዎች
የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከመልካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1054472341218 ገቢ በማድረግ ገንዘብ ገቢ የተደረገበትን የባንክ ስልፕ በመያዝ ወደ መልካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመሄድ የገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን ከመልካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- በፌዴራል ገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በባንክ የተመሰከረ የጨረታ ማስከበርያ CPO 250,000 (ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- በማሽነሪ ኪራይ ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም ተጫራች በሚያቀርባው ዋጋ ላይ የነዳጅ፤ የመኪና ቅባት፤ የጥገና፤ የሹፌርና የረዳት የውሎ አበል እና ሌሎች ተዛማች ወጭዎችን በተጫራቹ (በአከራይ) ድርጅት የሚሸፈን ይሆናል፡፡
- ተጫራች ጨረታውን ካሸነፋ በኋላ ማሽነሪዎችን በራሱ ወጪ መልካ ኖኖ ከፍለ ከተማ መስሪያ ቤት ባዘጋጀው የልማት ቦታ (ሥራ የሚሠራበት ቦታ) ድረስ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ላይ የሚያቀርበው ማሽነሪ ወይም የፒካፕ መኪና ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ የባለቤትነት ማስረጃ ወይም ሊብሬ ወይም ሕጋዊ የከራይ ውል አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበርያ ዋስትና 10% ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራች የሚወዳደርበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በትክክል በማሙላት ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የመንግስት የሥራ ቀናት ውስጥ በመልካ ኖኖ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for renting road construction machinery (dozers, excavators, graders, loaders, rollers, dump trucks, showers, lowbeds) and various pickup trucks for the 2019 budget year. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
