Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address መ/አምባ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113360162
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 400 /አራት መቶ ብር ብቻ
  • opening dateበ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Categories Construction and Water Works , Building Construction , Construction Works

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በትምህርት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የደሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ክፍል (አንድ ብሎክ) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር

GGWW/0003/2019

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በትምህርት ጽ/ቤት አማካይነት ለሚያሰራው የደሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አራት ክፍል (አንድ ብሎክ) ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች

  1. የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ የመወዳደሪያ ደረጃቸው ደግሞ GC/BC ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች፡፡
  2. ከገቢዎች መስሪያ ቤት የአዲስ ከሊራንስ ማምጣት የሚችሉ
  3. ተወዳዳሪዎች የቫት 7.5% ተቀናሽ ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን አለባቸው
  4. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ የድርጅቱ ባለቤት መሆን አለባቸው እንዲሁም በውክልና ሰነዱን መውሰድና መወዳደር አይቻልም፡፡
  5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር ብቻ በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መሀል አምባ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር በገ/ጉ/ወ/ወ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴክኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 (ሀያ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. የጨረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም፡፡
  2. ተጫራች ተጫርተው ከሸነፉ በኋላ አገልግሎታቸው ጥራት ያለውና ቀልጣፋ ካልሆነ የውል ጊዜን የምናቋርጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  3. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  4. ተወዳዳሪዎች ከአሸነፉ በኋላ ቅድመ ክፍያ ሳይጠይቁ ስራውን መስራት የሚችሉ መሆን፡፡
  5. በወረዳው ውስጥ አንድም ፕሮጀክት የያዘ አካል መወዳደር አይችልም፡፡

ለበለጠ መረጃ- የገ/ጉ/ወ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ስልክ ቁጥር 0113360631/146 ይደውሉ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for constructing a four-classroom block at Desa Secondary School in Gedebano Gutazer Wolene District, financed by the 2019 budget. Bidders need valid licenses, VAT/TIN registration, and GC/BC grade 6 or higher.
Save Tender