Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ምዕ ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ኮንታ ዞን ከጅማ ከተማ በስተ ደቡብ 102 ኪ. በአመያ ከተማ ፡ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0917388691
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Price500 (አምስት መቶ) ብር
  • opening dateበዚህ ዕለት 8፡30 ሰዓት
  • Categories Construction and Water Works , Building Construction , Construction Works

በደ/ምዕ ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለኮንታ ዞን ግብርና አከባቢ ጥበቃና ልማት መምሪያ የእህል ማከማቻ መጋዝን ግንባታ በ2019 በጀት ዓመት በካፒታል ፕሮጀክት GC/BC ደረጃ -5 እና ከዛ በላይ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለኮንታ ዞን ግብርና አከባቢ ጥበቃና ልማት መምሪያ የእህል ማከማቻ መጋዝን ግንባታ በ2019 በጀት ዓመት በካፒታል ፕሮጀክት GC/BC ደረጃ -5 እና ከዛ በላይ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ስመጫረት የምትፈልጉ፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፤
  3. ግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
  4. የመንግሥት ግዥ ላይ አቅራቢነት ሰርተፍኬት
  5. ተጨማሪ እሴት ታክስ
  6. የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
  7. የግብር ዘመኑ ከዕዳ ነፃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ታክስ ክሊራንስ
  8. መልካም ሥራ አፈፃፀም የ2016 ወይም 2017 ዓ.ም ወይም 2018 ዓ.ም ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡ በ2018 ዓ/ም ፍቃድ ያወጡትን የመልካም ሥራ አፈፃፀም አይመለከታቸውም፡፡
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ብቻ ከታወቀ ባንክ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ይህን ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ ተከታታይ 15ኛው ቀን ድረስ ከኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጨረታ ዶክመንት በመግዛት እና ዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴክኒካል ኦርጅናል 1 እና ቴክኒካል ኮፒ 1፤ ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ፋይናንሻል ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማደረግ በእናት ፖስታ በማሸግ በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚህ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ወስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  11. በተራ ቁጥር 9 መሠረት የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚህ ዕለት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ይከፈታል፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል ከኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 9 መውስድ ይኖርባቸዋል፡፡
  13. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፁት መስፈርቶችን የማያሟላ ተጫራች ለቴክኒካል ግምገማ የማያልፍ ሲሆን መስፈርቱን ያሟላ ተጫራች ወደ ቴክኒካል ግምገማ የሚቀርብ ይሆናል፤
  14. በዚህ በቅድመ ግምገማው ላይ ያልተገለፁ መስፈርቶች በዋናው ተጫራቾች መምሪያው ላይ ተመላክቷል፡፡
  15. ሂሳብ ስህተት ከተነበበው ጠ/ዋጋ ከ5% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ በግዥ መምሪያ ተግባራዊ ይደረጋል፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 7.5% እና የዊዝሆልዲንግ 3% ክፍያ ስርዓት ተግባራዊ ይደርጋል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ፡ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0472270007/0917388691/0917161785/0935138008 መደወል ይችላሉ፡፡

በደ/ምዕ/ኢት/ያ/ሕ/ክ/መ/የኮንታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for construction of a grain storage warehouse for Konta Zone Agriculture Office, requiring GC/BC grade 5 or higher contractors. Bidders must hold valid trade license, registration, tax clearance, VAT, and renewed competency certificate.
Save Tender