Tender Detail

Tender Details

  • Company የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address ሚዛን አማን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0471355629
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 2:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ (non-refundable)
  • opening dateይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት
  • Categories Vehicles Rent , Transportation Service And Cargo

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በሎት 1፡- የሰራተኞች መኪና ሰርቪስ ኪራይ ግዥ፣ በሎት 2፡- የጭነት አገልግሎት ኪራይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል በሎት 1፡- የሰራተኞች መኪና ሰርቪስ ኪራይ ግዥ፣ በሎት 2፡- የጭነት አገልግሎት ኪራይ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው (tin no) ያላቸው፣
  3. የዘመኑን የቴክኒክ ምርመራ አልፎ ቦሎ ያለው።
  4. የተሟላ የመድን ሽፋን ዋስትና ያለው።
  5. የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ።
  6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
  7. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከገቢዎች መ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፣ ሎት 1፡- የሰራተኞች መኪና ሰርቪስ ኪራይ ግዥ ብር 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 2፡- የጭነት አገልግሎት ኪራይ ግዥ ብር 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
  11. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣው 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ሁለቱም ጨረታ ፡- ማለትም ሎት 1 እና ሎት 2 የቫት ተመዝጋቢ ባይሆኑም መሳተፍ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 047 135 5629

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for hiring staff vehicles (Lot 1) and cargo transport services (Lot 2) for sector offices in Bench Sheko Zone. Bidders need valid trade license, TIN, technical inspection, insurance, ownership documents, and tax clearance.
Save Tender