Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address centeral reginal state , Phone: 0921542357/0926928268
  • Website
  • Deadline05 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200/ሁለት መቶ/
  • opening dateየዛኑ ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Categories Stationery Materials , Vehicle tire

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእምድብር ከተማ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ በሎት የተከፋፈሉ ማለትም ሎት 1 የእስቴሽነሪ አይነቶች ሎት 2 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ /001/2018

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለእምድብር ከተማ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ በሎት የተከፋፈሉ ማለትም ሎት 1 የእስቴሽነሪ አይነቶች ሎት 2 የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. በንግድ ዘርፉ የተሰማራችሁ ተወዳዳሪዎች የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ቲን ነበር እና የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦን ላይን /EGP/ መመዝገባችሁን ማረጋገጫ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባችሁ፡፡
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታው ሰነድ እያንዳንዱ በምትወዳደሩበት ሎት ላይ በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ የእምድብር ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በመከፈል ሰነዱን በእምድብር ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ ክፍል በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንታችሁ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከላይ በተራ ቁጥር ላይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎች ኦርጅናል ሰነድና ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባችሁ፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ /15/ አስራ አምስት/ ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን እስከዛ ድረስ የጨረታ ዶክመንታችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።
  5. ጨረታው የሚያበቃው የመጨረሻው ቀን ከቀኑ 8፡00 /ስምንት/ ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጎ የዛኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 /ስምንት ሰዓት ተኩል/ ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታው ለመከፈት የሚያግድ ነገር የሌለ መሆኑን እየገለጽን በዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ለሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል፡፡
  6. ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በምትወዳደሩበት እያንዳንዱ ሎት ላይ 25,000 /ሃያ አምስት/ ሺህ ብር በእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0921542357/0926928268

በጉራጌ ዞን የእምድብር ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender for stationery (Lot 1) and vehicle tires (Lot 2) for sector offices in Emdibir town, Gurage Zone. Bidders must be registered on EGP with valid trade license, TIN, VAT, and supplier certificates.
Save Tender