የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ለመሸጥ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 03/2018
የኢትዮጵያ ቱሪስት ንግድ ሥራ ድርጅት ንብረት የሆኑ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የታርጋ ቁጥር |
የተሽከርካሪ ዓይነት |
የሻንሲ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የተመረተበት ዘመን |
የሚይዘው የሰው ብዛት |
1 |
አ.አ 03-61394 |
Nissan Pick up |
ADNJ980000E006170 |
QD32-277413 |
2009 |
5 |
2 |
አ.አ 03-52805 |
Nissan Minibus |
JN1TG4E25ZO-784710 |
ZD30-209097K |
2008 |
11 |
3 |
ኢት 03-51714 |
Bishoftu Pick up |
EBPH4C4B473001112 |
4JB1T1-40402839Z |
2014 |
5 |
4 |
አ.አ 03-86040 |
Toyota Pick up |
AHTFR22G006062522 |
2KD-5833102 |
2012 |
5 |
5 |
ኢ ት -04-08814 |
Toyota Pick up |
LN106.0087890 |
3L.3399716 |
1998 |
5 |
6 |
ኢት 03-10460 |
Toyota Pick up |
YN850055605 |
2Y-0788336 |
1993 |
5 |
7 |
ኢት -03-12682 |
Toyota Pick up |
YN85-00555599 |
2Y-0788240 |
1998 |
4 |
8 |
ኢት -03-10473 |
Toyota Automoble |
KE706206295 |
4K-6572619 |
1986 |
5 |
9 |
ኢት -03-12680 |
Toyota Minibus |
RZH112-0004244 |
1RZ-0038936 |
1998 |
10 ኩንታል |
10 |
ኢት 03-10458 |
Mitsubishi Pick up |
JMY]NK-340WP01568 |
4D56KC8516 |
2000 |
5 |
11 |
ኢት 03-15051 |
Toyota Minibus |
0021962 |
1477886 |
1998 |
11 |
12 |
ኢት 3-51715 |
Bishoftu Medibus |
EBDHM324051000078 |
2014D000403 |
2014 |
32 |
13 |
ኢት 3-28907 |
HUNDAYE / Van |
KMCGKRAFP6CO27483 |
D4AF-5261563 |
2005 |
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሠነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሃያ ሁለት ማዞሪያ በሚገኘው የድርጅቱ ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ መሸጫ የማይመለስ ብር 500.00 / አምስት መቶ ብር/ ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ከነሐሴ 27 ቀን 2018 እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሜን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተሽከርካሪው ቀደም ሲል ያልተከፈለ የቦሎ እና የጉምሩክ ቀረጥ ግብር ወጪ ካለው ድርጅታችን የሚሸፍን ሲሆን የስም ማዘዋወሪያ፣ የትራንዚት እና ሌሎች ወጪዎች ግን በገዥው ይሸፈናል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የሚገዙት ተሽከርካሪ ብር 100,00 / አንድ መቶ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ የመገምገሚያ መስፈርት፣ ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ሲፒኦ/ እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ቦታ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ድርጅቱ ያወጣውን ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ተሽከርካሪውን በ10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
- ተሽከርካሪዎቹ የሚገኙበት ቦታ ሃያ ሁለት የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግቢ፣ አያት ደራርቱ አደባባይ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ እና ቦሌ ካርጎ ጎን በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ ውስጥ ነው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0914 34 13 42 / 0912 03 33 91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
