ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ይዘንጋዉ ማናዬ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዛቸዉንና ዝርዝር ሁኔታቸዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ለመጀመርያ ጊዜ የወጣ የኃራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ ለአቶ ይዘንጋዉ ማናዬ ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዛቸዉንና ዝርዝር ሁኔታቸዉ ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተገለጹትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የንብረቱ መገኛ፤ደረጃና ካርታ ቄጥር |
የጫረታዉ መነሻ ዋጋ |
1 |
አቶ ይዘንጋዉ ማናየ |
አቶ አቅናዉ ጌታቸዉ |
አ/አ ከተማ ቦሌ 9/99/6/15/44980/102041/01 G+3 መኖሪያ የቦታዉ ስፋት 150 ካ/ሜ |
29‚464‚171.14 |
2 |
አቶ ይዘንጋዉ ማናየ |
አቶ ወልዴ ተሸመ |
አ/አ ከተማ ለ/ኩራ/4/12/497/250296/1265/00 G+2 መኖሪያ የቦታዉ ስፋት 176 ካ/ሜ |
28‚075‚589.10 |
በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸዉ በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል፡፡
- ተጫራቾች የቤቱን/የተሸከርካሪዉን የጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጫረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጫረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል፡፡
- በጫረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ድርጅት ከሆነ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት፡፡
- የጫረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጫረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል፡፡ አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨራታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፡፡
- በጫረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸመል፡፡
- የጫረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ/ተሸከርካሪዉ ጋር የተያያዙ ማንኛዉንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ወጭዎችን ገዢ ይከፍላል፡፡ ማንኛዉም ዉዝፍ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር ዉል እንዲዋዋል ይደረጋል፡፡
- ተጫራቾች ቤቱን እና ተሸከርካሪዉን በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ፡፡
- ጫረታዉ የሚካሄደዉ መስከረም 20/2019 ዓ ም ከጠዋቱ 3.00 እስከ 6.00 ሰዓት ጫረታ በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል፡፡
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ፡- ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251115582978 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
