Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 0335510693
  • Website
  • Deadline01 Sep 2026, 9:50 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ)
  • opening date26/2018 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታዉ 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል)
  • Categories Vehicle , Goods

በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ dorco/ ምላጭ'አልባሳት፤ኮስሞቲከስ፣ አጎበር USB CABLE እና Hik Vision Network Camera በግልፅ እንድሁም ጫማ ፣ወንበር /office chair/፣ አልባሳት እና ተሽከርካሪ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል


 በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ dorco/ ምላጭ'አልባሳት፤ኮስሞቲከስ፣ አጎበር USB CABLE እና Hik Vision Network Camera በግልፅ እንድሁም ጫማ ፣ወንበር /office chair/፣ አልባሳት እና ተሽከርካሪ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-

 

1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋርተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የዘመነን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ከሊራንስ) እና የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሸከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ-18-አመት በላይ የሆነ የኗሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።

 

2) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋርተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስከር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብርከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።

 

3) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስከር ወረቀት (ሰርትፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገዉም፡፡

 

4) በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም፡፡

 

5) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03:00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡

 

6) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋበሚለው አምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይየተገለፁትን በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::

 

7) የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታው 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታዉ 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል፡፡

 

8) ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመከፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡በተሰጠው የጊዜገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ግቢ ተደርጎ እቃዉ እንደገና ለጨረታ ይቀርባል፡፡

 

9) ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሸናፊ ከሆነ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል፡፡

 

10) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡

 

11) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሐራጅ ጨረታ የእቃው መ ነሻ ዋጋ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 ሁለት መቶ ሺህ ብር እንድሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብርበታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 መቶ ሺህ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅዕ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

 

12) መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-033 551 06 93 ደውለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

                                                                           ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት

 

✨ messages.ai_summary
Sale of confiscated goods by Kombolcha Customs Branch: razors, cosmetics, USB cables, Hik Vision cameras via open tender; shoes, office chairs, clothing, and vehicles via auction. Bidders need relevant trade licenses, tax clearance, and VAT registration (except items under 2M birr). Individuals 18+ with ID may bid on vehicles.
Save Tender

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዋና ስራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት መጠቀሚያ የሚሆን በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰሩ ተሽ...

READ MORE