ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በአጋርነት በሚሠራው ፕሮግራም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስተዳደር እና በሲዳማ ክልል በዳራ እና ዳራ አቲልቾ ወረዳዎች ለሚያስገነባው የተማሪዎች መማሪያ ክፍል እና የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
ሪች ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ከፕላን ኢንተርናሽናል ጋር በአጋርነት በሚሠራው ፕሮግራም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን አረካ ከተማ አስተዳደር እና በሲዳማ ክልል በዳራ እና ዳራ አቲልቾ ወረዳዎች ለሚያስገነባው የተማሪዎች መማሪያ ክፍል እና የመፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት፡-
- በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው
- GC/BC-5 ደረጃ እና በላይ ከከተማ ልማት ሚኒስቴር የተመዘገቡና ፍቃድ ያሳደሱ
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ
- ከመንግሥት የሚፈለግበት ግብርና ታክስ ዕዳ አለመኖሩን የሚገልጽ ለበጀት ዘመኑ ብቻ የሚያገለግል የስምምነት ደብዳቤ ከሚመለከተው የታክስ አስተዳደር ቢሮ ማቅረብ የሚችል
- ወርሐዊ የታክስ ማሳወቂያ በማቅረብ የተሰበሰቡትን የተጨማሪ እሴት ታክስ ገቢ ማድረጋቸውን የሚገልጽ ከሚመለከተው ገቢዎች የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ 2% ሲፒኦ በማሠራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የሚያሟሉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ ብር ብቻ/ በድርጅቱ ስም ገቢ በማድረግ ደረሰኝ በመውሰድ የማስረጃዎቻቸውን ኦርጅናል ይዞ በመቅረብ በመመዝገብ ኮፒውን በማስያዝ ከድርጅቱ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የሚችሉ ሲሆን አንድ ኦርጂናልና ሁለት በፎቶ ኮፒ ማሽን ኮፒ የተደረጉ ሰነዶችን እያንዳንዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቬሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14/አስራ አራት/ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጠዋቱ 2:30-6:30 ከሰዓት ከ7:30-11:30 ሰዓት ድረስ ዲላ በሚገኘው ሪች ዘ ኒዲ (RTN) ኢትዮጵያ ዋና ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በሰነዱ ላይ የፕሮጀክቱን አገልግሎት ዋጋ በአኃዝና በፊደል በግልጽ መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- በኦርጅናል ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የተቋራጩ ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፡፡
- በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶችን ማቅረብ ከጨረታው ውጪ ያደርጋል፡፡
| ተ.ቁ | የግንባታው ዓይነት | LOT | ግንባታው የሚገነባበት ወረዳና ቀበሌ |
| 1 | 1-ብሎክ ባለ 4-ክፍል የተማሪዎች መማሪያ እና 6-ክፍል ያለው 1-መፀዳጃ ቤት | LOT1 | ሳቴ ሀንጋላ /ዳራ ወረዳ (Sate hangela Dara) |
| 2 | LOT2 | ሺልቾ/ዳራ-ኦቲልቾ ወረዳ (Dara otilicho) | |
| 3 | LOT3 | ዶላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት/አረካ ከተማ አስተዳደር (Areka town Administration) |
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 6:30 ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አንዱ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ከላይ የቀረቡትን መስፈርቶች ሳያሟሉ የሚያቀርቡ ተቋራጮች ከጨረታው ውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0463310049 / 0463313145
ሪች ዘኒዲ ኢትዮጵያ
✨ messages.ai_summary
Reach the Need Ethiopia seeks contractors to build student classrooms and latrines in Wolaita Zone, Areka town, and Sidama Region's Dara and Dara Otilcho districts. Bidders need renewed trade licenses, GC/BC-5 registration, VAT certification, tax clearance, and performance records.
