Tender Detail

Tender Details

  • Company የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
  • Address በታርጫ ከተማ ከቴሌ ቢሮ በስተጀርባ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-04-69-39-79
  • Website
  • Deadline14 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Price500 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateበዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት
  • Categories Building Materials , Building Construction , Construction Works

በደ/ምዕ/አ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም በጀት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የጨልሾ የእንስሳት ጤና ኬላ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ፤ አንድ የእንስሳት ማዳቀያ ግንባታ እና ዙሪያ አጥር ስራ በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡


ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/አ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በአውሮፓ ህብረት አደጋ ቅነሳ ፕሮግራም በጀት በዳውሮ ዞን ማሪ ማንሳ ወረዳ የጨልሾ የእንስሳት ጤና ኬላ አንድ ብሎክ ህንፃ ግንባታ፤ አንድ የእንስሳት ማዳቀያ ግንባታ እና ዙሪያ አጥር ስራ በ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት ስመጫረት የምትፈልጉ -

  1. በዘርፉ ለ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ያለው
  4. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN no) ያለው
  5. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት
  6. ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተሠጠ የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችልና ደረጃውን በተመለከተ 5 (አምስት) እና ከዛ በላይ GC፣ BC መሆን አለበት፡፡
  7. ከማንኛውም ታከስ ዕዳ ነፃ ስለመሆኑ ከባለስልጣኑ መ/ቤት የታክስ ከሊራንስ በ2018 ዓ.ም የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል፡፡
  8. የመልካም ሥራ አፈጻጸም (Good Performance Certificate) ከዚህ ቀደም ተመሳሳይየመንግሥት ወይም መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ላይ የሰራበትን የሚያሳይ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል።
  9. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) CPO /የባንከ ጋራንቲ⁄ ጥሬ ገንዘብ ከታወቀ ባንከ በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ስም በማዘጋጀት በቴክኒካል ኦርጅናል ዶከመንት ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት ግዥ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) ብቻ በአካውንት ቁጥር 1000521691305 በማስገባት የባንክ አድቫይስ ይዞ በመምጣት በዳውሮ ዞን ተርጫ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነድ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ የደ/ም/ኢት/ህ/ከ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬከቶሬት ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ዶከመንቶች በመግዛትና በዋጋ ማቅረቢያ በመሙላት ቴከኒካል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 1 ፋይናንሻል ኦርጅናል 1 እና ኮፒ 2 በድምሩ 5 ፖስታ የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ በአንድ እናት የጨረታ ፖስታ ውስጥ በማስገባት የደ/ም/ኢት/ህ/ከ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  12. ተጫረቾች በእያንዳንዱ ዶክመንት ላይ በመፈረም ማህተም በማድረግ በፖስታ ጀርባው ላይበሚታይ ጽሑፍ ኦርጅናል እና ኮፒ ለይቶ መጻፍ አለበት፡፡
  13. የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው በ22ኛው ቀን ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሸጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ም/ኢት/ህ/ከ/መንግስት አደጋ ስጋት ስራ እመራር ኮሚሽን ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡
  14. በጨረታ ማስታወቂያ ያልተገለጹ ሌሎች የመወዳደሪያ ነጥቦች (መስፈርቶች) በጨረታ ዶክመንቱ መሠረት ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  15. ተጫራቾች unconditional letters (በሁኔታ ላይ ያልተገደበ ደብዳቤ) ከታወቀ ባንክማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  16. የሂሳብ ስህተት ከጠቅላላ ድምር ከፍታ እና ዝቅታ 5% በመመሪያው መሠረት ተግባራዊ ይሆናል፡፡
  17. በጨረታ ማስታውቂያ እና ዶክመንቱ ላይ የተገለፁትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ተጫራች ብቻ ወደ ድህረ ግምገማ ያልፋል፡፡
  18. ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቦታው ላይ ያለመገኘት የጨረታ አከፋፈትን አያስተጓጉልም፡፡
  19. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበስጠ መረጃ፡- በቢሮ ስልክ ቁጥር፡-0920925053

አድራሻችን- በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ ውስጥ የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ቢሮ ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 145 ኪ.ሜ ከወላይታ ሶዶ ከተማ በስተምዕራብ 165 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በታርጫ ከተማ ይገኛል፡፡

በደ/ምዕ/ኢ/ህ/ክ/መ/ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን

✨ messages.ai_summary
Construction of one animal health post block, one animal insemination facility, and perimeter fencing in Mari Mansa district, Dawro Zone, funded by the EU disaster risk reduction program. Bidders need renewed trade licenses, tax clearance, and Ministry of Construction certificates (GC/BC grade 5 or above).
Save Tender