Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address በስልጤ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 882 0005
  • Website
  • Deadline12 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 500 /አምስት መቶ ብር/
  • opening dateባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Categories Building Construction

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለስልጤ ለዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ሼድ ግንባታ ለማሠራት በመስኩ የተሰማሩ ማኅበራትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለስልጤ ለዞኑ ባህል ቱሪዝም መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ሼድ ግንባታ ለማሠራት በመስኩ የተሰማሩ ማኅበራትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል። ስለሆነም ደረጃቸው B.C/ G.C-9 እና ከዛ በላይ የሆኑ፤

*        የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ፤

*        የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፤

*        የታደሰ የንግድ ፈቃድና የስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤

*        ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸውን የዘመኑን የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ፤

*        የጨረታ ዋስትና 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችሉ፤

*        የኦዲት ሪፖርት እና የድርጅቱን አወቃቀርና ከዚህ በፊት የሠሯቸውን ሥራዎች የሚገልፅ የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች ሰነድ ለየብቻ ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻል ዶክመንቱን በሚገባ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ፣ ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦሪጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡ 20ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

*        ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

*        የተወዳዳሪ ተቋራጮች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መክፈቻ ቀኑን አይለውጥም።

*        መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 046 771 0586 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Open tender for construction of sheds for the Silte Zone Culture and Tourism Department. Eligible bidders must hold BC/GC-9 or higher, with renewed licenses, tax clearance, VAT registration, and relevant work experience.
Save Tender