Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
  • Address ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነኦ ሆስፒታል አጠገብ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251115579684
  • Websitehttps://etsugar.com/esig/
  • Deadline21 Sep 2026, 4:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ)
  • opening date8. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው::
  • Categories Equipment And Accessories , Construction Machinery , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ባለሰንሰለት ሃይድሮሊክ ኤክስካቫተር ማሽን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


ባለሰንሰለት ሃይድሮሊክ ኤክስካቫተር ማሽን ግዥ ብሔራዊ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፦ አሸጨ/0015/ኦኩስፋ-2/2018 ዓ.ም

  1. በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ባለሰንሰለት ሃይድሮሊክ ኤክስካቫተር ማሽን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
  2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የ120 ቀን የባንክ ዋስትና /BID BOND/ በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ተጫራቾች በመንግስት ግዥ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር /supplier List/ ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በተጨማሪ የበጀት ዓመቱን ታክስ ክሊራንስ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀን ውሎ በአስራ ስድስተኛ ቀን ይከፈታል፡፡ የጨረታውን መከፈቻ ትክክለኛ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
  4. ብቁ ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ ለሁሉም የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡00-6፡00) ቀጥሎ በተመለከተው አድራሻ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. የጨረታው ሰነድ የሚሸጥበት፣ ለውድድር የቀረበ ሰነድ የሚገባበትና የሚከፈትበት አድራሻ ቀጥሎ በተመለከተው ነው፡፡

5.1. ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ የስኳር ፋብሪካዎች ማስተባበሪያ ቢሮ ቶታል ሶስት ቁጥር ማዞሪያ 300 ሜትር ከፍ ብሎ ተዘነአ ሆስፒታል አጠገብ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ፡፡ ስልክ ቁጥር፡ 09-91-14-94-85/0986862766/ 0940209464 አዲስ አበባ/ ኢትዮጵያ

  1. ተጫራቾች ለሁሉም ሎቶች አንድ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. የዕቃው ርክክብ የሚፈፀመው ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ የሚገኝበት ማለትም ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ኃይል ውሃ ቀበሌ ነው፡፡
  3. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ለ28 ቀናት ነው፡፡
  5. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ
Tel 0940209464 ኃይል ውሃ

አዲስ አበባ ግዥ ማስተባበሪያ ቢሮ
Tel: 09-91-14-94-85/0986862766 አዲስ አበባ

በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር-2 ስኳር ፋብሪካ

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Sugar Industry Group's Omo Kuraz-2 Sugar Factory seeks to procure a crawler hydraulic excavator machine through a national open tender. Eligible bidders must provide a CPO or bank guarantee, valid business license, tax clearance, VAT registration, and supplier list certification. Delivery is to South Ethiopia Regional State, South Omo Zone, Hayl Woha Kebele.
Save Tender