በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ሶስት አርቲኩሌትድ ትራክተር ኪራይ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚታሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለሁለተኛ ዙር የወጣ ብሔራዊ የጨረታ ቁጥር፡-LP/OT/OC
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ጽ/ቤት ሶስት አርቲኩሌትድ ትራክተር ኪራይ የአገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚታሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሰነድ ጋር ህጋዊ የታደሰ አዲስ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከሚመለከተው አድራሻ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት (ከሰኞ እስከ ዓርብ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-10፡30 እና ቅዳሜ ከሰዓት በፊት ከ2፡30-6፡00) ቀጥሎ ከተመለከተው አድራሻ በመቅረብ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ግዥ ቡድን (ማስተባበር ቢሮ)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 002/0KSF1&3/2018
አድራሻ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ፣ ከጦር ሃይሎች ወደ ዘነብ ወርቅ በሚወስደው መንገድ በተስምዶ 3 ቁጥር ማዞርያ / ቶታል ገባ ብሎ የፌድራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንፃ ላይ ሕ-B ቢሮ ቁጥር 1371/125 ፎቅ፡፡
ስልክ ቁጥር (አድራሻ) +251-963442882/+251-916170834
አዲስ አበባ
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሶስት አርቲኩሌትድ ትራክተር ኪራይ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጨረታው መከፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው 29/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 29/12/2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ነው፡፡
- የጨረታው ማስከበርያ ዋስትና ፀንቶ የመቆያ ጊዜ ለ60 ቀናት ነው፡፡ ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የኦሞ ኩራዝ 1 እና 3 ስኳር ፋብሪካ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for renting three articulated tractors for Omo Kuraz Sugar Factories 1 and 3. Bidders must be legally registered, tax-compliant, and listed with the Ministry of Finance or Public Procurement Agency.
