Tender Detail

Tender Details

  • Company አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀላፊነቱ የተወሰነ
  • Address አርባጉጉ የገ/ሕ/ሥራ/ ዩኒየን አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ : ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 21 09 68 80
  • Website
  • Deadline07 Sep 2026, 10:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • opening dateጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Vehicle

አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገለ አንድ ኤፌሰር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴሉ 2014 እና ሁለት ትሬሸሮች በትራከተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቦቸው 1200 የሆኑ ትሬሸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

አርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃ/የተወሰነ ያገለገለ አንድ ኤፌሰር የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት የሆነ ሞዴሉ 2014 እና ሁለት ትሬሸሮች በትራከተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቦቸው 1200 የሆኑ ትሬሸሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፦

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

  1. ለጨረታው የወጣ ኤፌሰር (FSR) የጭነት መኪና የጃፓን ስሪት ሞዴል 2014 የሆነ ተሽከርካሪ የሰሌዳ ቁጥር አአ-05-02431 መነሻ ዋጋ 6,500,000 (ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) እንገልፃለን ፡፡
  2. ሁለት ትሬሸሮች በትራከተር ተጎትቶ የተለያዩ ሰብሎችን የሚወቁ የቱርክ ስሪት የሆኑ ሱፐር ቱርቦቸው 1200 የሆኑት የአንዱ መነሻ ዋጋ 650,000 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሲሆን የሁለቱ ዋጋ አንድ ላይ 1,300,000 (አንድ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ብር) መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  3. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ከአርባጉጉ የገ/ሕ/ስራ/ዩኒየን/ጽ/ቤት መግዛት የምትችሉ መሆኑንና ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ወይም መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ግለሰብ ወይም የገበሬ አባል የሆነ የዘመኑ የናሽናል ID (የታደሰ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ) ማቅረብ እና ድርጅት ከሆነ የታደሰ የዘመኑ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለያንዳንዱ ለጨረታው ለቀረቡት ንብረቶች 10% CPO በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
  6. ለጨረታው ለቀረቡት ንብረቶች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 10፡00 (ሰዓት) ድረስ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ግቢ ውስጥ ሙገር አካባቢ ታደሰ አበበ ህንፃ ጀርባ ኤፌሰር የጭነት መኪናውን ማየት ይችላሉ፡፡
  7. ለጨረታው የቀረቡትን ሁለት ትሬሸሮች በአርሲ ዞን በጮሌ ወረዳ በአርባጉጉ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን መጋዘን ያለበት ግቢ ውስጥ በግልፅ ማየት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (ሰዓት) ጀምሮ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የአርባጉጉ የገ/ህብረት ስራ ዩኒየን አዳማ መጋዘን ተዘግቶ በ5፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  9. ጨረታው በ16ኛ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (ሰዓት) ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ እለት በ5፡00 (ሰዓት) ላይ ይከፈታል፡፡
  10. ተጫራቾቹ የግል ድርጅት ወይም የመንግስት ድርጅት ከሆነ የውከልና ደብዳቤ እና የናሽናል ID (የታደሰ የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ) ማቅረብ አለበት ፡፡
  11. ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ሙሉ ከፍያ ከፍሎ በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መውሰድ አለበት፡፡
  12. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በዩኒየኑ ጽ/ቤት በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0921096880/0920063165/0917034343 ደውለው መረዳት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

አድራሻችን፦ አርሲ ዞን መርቲ ወረዳ አቦምሳ ከተማ ዐ1 ቀበሌ መሆናችንን እንገልፃለን፡፡

አርሲ ዞን አርባጉጉ የገበሬዎች ሕ/ሥ/ዩኒየን ሀሳፊነቱ የተወሰነ

✨ messages.ai_summary
Arba Gugu Farmers Cooperative Union is selling one used FSR truck (Japanese, 2014 model) and two Turkish-made Super Turbo 1200 tractors with trailers via open tender. Bidders must provide valid ID or renewed business license and a 10% CPO bid security.
Save Tender