በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ፣ የተለያዩ ንብረቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ጎማዎች፣ የተለያዩ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች እና የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ፣ የተለያዩ ንብረቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ ጎማዎች፣ የተለያዩ ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች እና የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቶች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፣
- የኤጀንሲው አድራሻ፣ አዲስ አበባ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊትለፊት ጨፌ አናኒ ሕንፃ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 Floor) ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግሥት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3 floor) ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
- የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10፡30 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው መስከረም 08/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 10% /አስር ከመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ C.P.O የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመከተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ CPO ለማሠራት የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-1-15-57-70-27
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ
(ፌንፊኔ)
✨ messages.ai_summary
Open tender for sale of various decommissioned assets: scrap metals, tires, scrap corrugated sheets, and office furniture. Bidders must purchase tender documents and submit sealed price offers with a 10% CPO bid security.
