Tender Detail

Tender Details

  • Company በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣደት5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤቶች ህ/ሥ/ማህበር
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0907075030
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 3:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500 /አምስት መቶ ብር/
  • opening dateበ10፡00 ሰዓት
  • Categories Construction and Water Works , Building Materials , Construction Works

የኮንደሚኒየም የአጥር ሥራ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት በዘርፉ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ይጋብዛል።



የጨረታ መስታወቂያ
የጨረታ
ቁጥር፡ /ጥ/የጋ/መ/መ/001/18

በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣይት 5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤቶች //ማህበር የኮንደሚኒየም የአጥር ሥራ የእጅ ዋጋ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት በዘርፉ ብቃትና ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ይጋብዛል። የሥራው ዝርዝር 455 ሜትር Chain Link አጥር ሥራ፣ የኮንክሪት ከርብ ስቶን መሠረት ሥራ፥ የብረት አምድና ቢም ሥራ፣ የበር አምድ፣ የብረት ማጠናከሪያና የመገጣጠሚያ ሥራዎችን ማሠራት ይፈልጋል ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ

1. በዘርፉ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ያለው፤ የግብር ክሊራንስ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው::

2. ለሥራው የሚያስፈልጉ የመሥሪያ መሣሪያዎችን፣ የሥራ ቅደም ተከተል work schedule/ እና የሰው ኃይል ዝርዝር ማቅረብ የሚችል።

3. ተመሳሳይ የአጥር ሥራ ልምድ ያለው፤ የሚያስፈልጉ ሕጋዊ ሰነዶችን የሚያቀርብ፤ የሥራውን ጥራትና የተወሰነውን የሥራ ጊዜ ማሟላት የሚችል መሆን አለበት።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50.000 /ሃምሣ ሺህ/ በተረጋገጠ ባንክ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል።

5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 7 ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል አራብሳ ሳይት 5 ጥላ የጋ/መኖሪያ /ቤት መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰንድ ኦሪጅናልና ኮፒውን ፊርማና ማህተም ያለው በታሸገ ፖስታ 7 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው የመወዳደሪያ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት 8ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 930 ሰዓት ተዘግቶ 1000 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጥላ /ቤት ይከፈታል።

8. የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን ይሆናል።

9. የጨረታ አሸናፊዎች አሸናፊነቱ በጽሑፍ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ በጽ/ቤቱ በመገኘት የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውል ማስከበሪያ ያለ ቅድመ ሁኔታ ለግዥ የሚከፈል/Unconditional bank guarantee/ በማስላት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።

10. ሠርቶ የማስረከቢያ ጊዜ 60 ቀንና ከዚያ በታች መሆን አለበት።

11. ተጫራቾች የቴከኒከና ፋይናንሻል ፕሮፖዛሎችን ዋናውና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፤ ሆኖም ግን ለይቶ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።

12. የጨረታ ሰነድን ማባዛት ወይም አሳልፎ መስጠት አይፈቅድም

13. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት።

14. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።

15. ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ማሳሰቢያ ውድድሩ የሚካሄደው በነጠላ እና በጠቅላላ ይሆናል።

ለበለጠ  መረጃ፡-

አድራሻ፡ በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣደትበስልክ ቁጥር 0907075030 ይደውሱ።

 

 

በለሚ ኩራ /ከተማ ወረዳ 06 አራብሳ ሣደት5 ጥላ የጋራ ሕንፃ ቤቶች //ማህበር

 

 

 

✨ messages.ai_summary
Open tender for condominium fence construction: 455m chain-link fence, concrete curb stone foundation, steel columns/beams, gate posts, and reinforcement/welding works. Bidders must have legal license, tax clearance, relevant experience, and submit work schedule and equipment list.
Save Tender