ተቋማችን በአዲስ አበባ ጎፋ በሚገኘው ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት ግቢ ውስጥ ላስገነባው የሠራተኞች ካፍቴሪያ እና ለመሰብሰቢያ አዳራሽ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዘመናዊ ፈርኒቸሮችን ግዥ እና ወልቂጤ ከተማ የሚገኘውን የኮንክሪት ምሰሶ ማምረቻ ንብረቶችን፤ ለመንቀል፣ ለማንሳትና ወደ ምትክ ቦታ ለማዛወር የአገልግሎት ሥራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ግፅ-004/2018 ሎት-1 እና ሎት-2
ተቋማችን በአዲስ አበባ ጎፋ በሚገኘው ማዕከላዊ ዕቃ ግምጃ ቤት ግቢ ውስጥ ላስገነባው የሠራተኞች ካፍቴሪያ እና ለመሰብሰቢያ አዳራሽ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዘመናዊ ፈርኒቸሮችን ግዥ እና ወልቂጤ ከተማ የሚገኘውን የኮንክሪት ምሰሶ ማምረቻ ንብረቶችን፤ ለመንቀል፣ ለማንሳትና ወደ ምትክ ቦታ ለማዛወር የአገልግሎት ሥራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
| ሎት | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
| 1 | ዘመናዊ የከበብና መሰብሰቢያ አዳራሽ ፈርኒቸር ግዥ | 75,000.00 | ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት | ጳጉሜ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
| 2 | የኮንከሪት ምሰሶ ማምረቻ ንብረቶችን ለመንቀል፣ ለማንሳትና ወደ ምትክ ቦታ ለማዛወር የአገልግሎት ሥራ ግዥ | 165,000.00 | ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት | ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታከስ ከሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መሥሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ:- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መሥሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መሥሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል ስልክ ቁጥር 011-156-01-48
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና “ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY" በሚል መሆን ይኖርበታል፤
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና መ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Procurement of modern furniture for a staff cafeteria and assembly hall in Addis Ababa, and relocation services for concrete pole production assets in Wolkite. Two lots: furniture supply and asset dismantling/relocation. Bidders must hold valid licenses, tax clearance, and VAT registration.
