Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት
  • Address አዋሽ ፡ አፋር ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09-13-97-49-27
  • Website
  • Deadline02 Sep 2026, 9:45 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price100 (አንድ መቶ) ብር
  • opening date27/12/2018 እና 30/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00
  • Categories Other , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት - 27/12/2018 እና 30/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት - 27/12/2018 እና 30/12/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፣ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣሎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣሎትማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች-

1.      ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ (clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴያቸዉን ለታከስ ማዕከሎ ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምስከር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣

2.    ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት አስከ ቀን 27/12/2018 እና 30/12/2018 ዓ/ም እስከ ጠዋቱ 3፡45 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽጤቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3.    ለግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5 በመቶ እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተዉ በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4.    ተጫራቾች በሚከተለዉ የጨረታ ቀናት (እስኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የጨረታ ቦታ

 

የጨረታው ዓይነት

 

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

 

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

 

የጨረታዉ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

1

 

ቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት

 

ግልጽ ጨረታ እና በሐራጅ

 

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ የመኪና መለዋወጫ፡ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፡ ኤሌክትሮኒክስ፣ ምግብ ነክ፣ የስፖርት እቃዎች፣ የእጅ ሰዓት፣ ኮስሞቲክስ፣ መነፅር፣ ጌጣ ጌጦች፣ የሳሙና ፋብሪካ አካል ማሸነሪ፣ እምነበረድ ድንጋይ፣ መሰላል ብረቶች እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች።

 

ለግልጽ ጨረታ 27/12/2018 እና 30/12/2018 እስከ ጠዋቱ 3፡45  

 

ለግልጽና ለሐራጅ ጨረታ 27/12/2018 እና 30/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡0ዐ ሲሆን የሐራጅ ጨረታ የመጀመሪያ ጊዜ 27/12/2018 እና 30/12/2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ይሆናል።

 

 

 

5.    የጨረታው መክፈቻ ቦታ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6.    ለጨረታዉ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋስትና ያስያዙት (cpo) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሥራ ቀናት ዉሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

7.    ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ዉሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።

8.    ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበዉ ያልወሰ ተጫራቾች በጨረታዉ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9.    ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Awash Customs Office seeks bidders for the open and auction sale of various contraband goods seized under customs law, including shoes, clothing, car parts, mobile phones, electronics, food items, and more. Bidders must meet eligibility requirements such as valid trade license, VAT registration, and tax clearance.
Save Tender