Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የቢሮውን አገልግሎት ለማዘመን የሶፍትዌር ልማት (Software Development) ማሰራት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 2019 በጀት ዓመት የቢሮውን አገልግሎት ለማዘመን የሶፍትዌር ልማት (Software Development / ለማሰራት ይፈልጋል በመሆኑም የሶፍትዌር አልሚ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ በጋዜጣ በማውጣት አጫርቶ ሶፍትዌር ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።

1)     ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT /ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።

2)     ተጫራቹ በባለፉት 3 (ሶስት) ተከታታይ ዓመታት በእያንዳንዱ ዓመት ቢያንስ 4,000,000 ብር የአመታዊ አማካይ ሽያጭ መጠን መኖር አለበት። ይህ ማለት በአጠቃላይ ቢያንስ 12,000,000 ብር የሶስት ዓመት ሽያጭ መኖር አለበት። ፍቃድ ባለው ኦዲተር የተረጋገጡ የፋይናንስ ሪፖርቶች መቅረብ አለባቸው።

3)     ተጫራቹ ድርጅት በሶፍትዌር ልማት ዘርፍ ቢያንስ 6 (ስድስት) ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያለው መሆን አለበት።

4)     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አጠቃላይ የሚያቀርበትን የፋይናንስ ጥቅል ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት / CPO/ ማቅረብ አለባቸው።

5)     ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ሣር ቤት የሚገኘው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት  እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 1 ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 1,000.00 /አንድ ሺህ ብርበመክፈል መግዛት ይችላሉ።

6)     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጂናልና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ፓስታ በማሸግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 430 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7)     ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ 10ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 500 ሰዓት ይከፈታል በዕለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።

8)     ቢሮ የሚያሰራውን ሥራ 20% የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9)     ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ሥራውን በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ : በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሣር ቤት

በሚገኘው ህንፃ 1 ፎቅ

የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ነው

ለተጨማሪ ማብሪሪያ

በስልክ ቁጥር 0911631348/0913152039/0917805333 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ኢንቭስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ

✨ messages.ai_summary
The Oromia Investment and Industry Bureau seeks software development services to modernize its operations. Eligible bidders must hold a valid license, VAT registration, and at least six years of software development experience, with audited financial reports showing minimum annual sales of 4,000,000 birr over three years.
Save Tender