ኖብል አክሽን ሆሊስቲክ ዴቬሎፕመንት የተባለ ግበረሰናይ ድርጅት ሁለት ያገለገሉ /አንድ ሀዮንዳይ አዉቶሞበል የቤት መኪና እና አንድ ፎርድ ባለሁላት ገቢና ፕክአፕ/ መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኖብል አክሽን ሆሊስቲክ ዴቬሎፕመንት የተባለ ግበረሰናይ ድርጅት ሁለት ያገለገሉ /አንድ ሀዮንዳይ አዉቶሞበል የቤት መኪና እና አንድ ፎርድ ባለሁላት ገቢና ፕክአፕ/ መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች አሟልተዉ እንዲጫረቱ ተጋብዘዋል፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ጥሪ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር የሥራ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ብቻ ለቡ ኮሜረሽያል 4ኛ ፎቅ ከሚገኘዉ ከኖብል አክሽን ሆሊስቲክ ዲቨሎፕመንት ቢሮ ቁጥር Q02 የጨረታ ሠነዱን በ500 ብር መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለአንድ መኪና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረገጋጠ ሲ.ፒ.ኦ/ በማስያዝ ከመጫረቻ ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ይህ ጨረታ የሚከፈተው በቀን ነሐሴ 29/12/2018 ዓ.ም ከሠዓት በኋላ 11፡00 ሠዓት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሐሴ 30 ቀን 2018 ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ላይ በድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል።
- ወድድሩ በይፋ በጨረታ የሚሸጥ ስለሆነ ማንኛዉም ህጋዊ ሠዉ መሳተፍ ይችላል።
- የጨራታው መነሻ ዋጋ በጨራታ ሠነዱ ውስጥ የተገለጸ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊነተቸው በተገለጸ አስር ቀናት ውስጥ ሙሉ ገንዘብ ገቢ አድርገው መኪኖችን የማንሳት ግዴታ አለባቸዉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ኖብል አክሽን ሆሊስቲክ ዲቨሎፕመንት
ለቡ ቫርኔሮ ኮርሺያል ማዕከል, 4ኛ ፎቅ
ቢሮ ቁጥር፡ Q02
ወረዳ 01, የቤት ቁጥር አዲስ
ነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ
ከለቡ መብራት በስተምዕራብ/ጀሞ አቅጣጫ በግምት 300 ሜትር
አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር፡ +251910436207፣ +251930303877፣ +251930303878
