ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለድርጅታችን የሥራ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ ፡- ሎት 1፡- የተለያዩ የኔትዎርክ ዕቃዎች (Different Network Devices) እንዲሁም ሎት 2፡- CCTV Surveilance System, Laptop Computer, Desktop Computer, Heavy duty Copier, Printer, projector …
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
CN/NCB/03/19
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል/ማህበር ለድርጅታችን የሥራ አገልግሎት ላይ መዋል የሚችሉ ፡-
ሎት 1፡- የተለያዩ የኔትዎርክ ዕቃዎች (Different Network Devices) እንዲሁም
ሎት 2፡- CCTV Surveilance System, Laptop Computer, Desktop Computer, Heavy duty Copier, Printer, projector …
ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 ከሠዓት 7፡00-11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00) ማግኘት ይቻላል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000 ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ያሸነፈው ተጫራች የዕቃዎች ርክክብ የሚደረግበት ቦታ ገርጂ የድርጅቱ የዕቃ ግምጃ ቤት ይሆናል፡፡ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
