Tender Detail

Tender Details

  • Company ይሓ ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር
  • Address , Phone: 0922079575
  • Website
  • Deadline03 Sep 2026, 4:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን ጋዜጣ
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • opening dateበ8 (ስምንተኛው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Categories Other , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

ይሓ ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን የኤሌክትሪክ እቃዎችን ባለ 36 እና 18 ዋት ሆልደሮች፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ የቧምቧ እቃዎች፣ የሊፍት እቃዎች፣ የጀነሬተር እቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያና ልዩ ልዩ እቃዎች፣ የመካኒካል እቃዎች፣ የእንጨት በር፣ የእንግዳ ወንበሮች፣ የአልሙንየም በሮች፣የአልሙንየም ፍርግርግ ብረቶች፣ የስፓይራል ብረት ከነመወጣጫው ብረቶች፣ የመኪና መከላከያ ብረት፣ ልዩ ልዩ እቃዎች እንዲሁም የተለያዩ የመኪና እቃዎች በግልፅ ጨረታ አጫርቶ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶች በማሟላት መጫረት ይችላሉ።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-

1.      የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300ን/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ፋይናንስ ክፍል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይችላሉ።

2.    ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሥም ሲፒኦ(CPO) ማቅረብ ይኖርበታል።

3.    ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ከኮድ 1 እስከ ኮድ 10 የተያያዙ እቃዎች የእቃዎችን ዝርዝር በማየት ለእያንዳንዳቸው በጥቅል ወይም ለየብቻ የሚገዙበት ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ።

4.    ተጫራች አሸናፊ መሆኑን በስልክ ከተነገረው እና ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ በአምስት የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ ወደ ድርጅቱ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ ክፍያውን ከፍሎ እቃዎቹን በተጠቀሱት ቀናት ማንሳት ይኖርበታል።

5.    ተጫራች ጨረታውን አሸናፊ መሆኑን ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ክፍያውን ከፍሎ እቃዎቹን ለማንሳት በተራ ቁጥር 4 በተጠቀሱት የሥራ ቀናት ውስጥ ለመቅረብ ፍቃደኛ ሳይሆን ቢቀር ያስያዘው CPO ለይሓ ሪል እስቴት ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሂሳብ ገቢ ይሆናል።

6.    ጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ 7(ሰባተኛው የሥራ ቀን) ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ይሆናል።

7.    ጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ8 (ስምንተኛው የሥራ ቀን) ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ይሆናል።

8.    ተጫራች የሚያቀርበውን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ የታሸገ ሲሆን፣ በኢንቨሎፑ ላይ የተጫራች ማንነት መግለጽ ይኖርበታል።

9.    ተጫራች ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ካላሟላ ከጨረታው የሚሰረዝ ይሆናል።

10.   ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ መገኘት ይችላል።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ስቴድየም ቤተዛታ ሆስፒታል ፊት ለፊት “ይሓ ሲቲ ሴንተር” ህንጻ

ስልክ ቁጥር- የቢሮ 011 558 0129 / 011 557 6954

ማሳሰቢያ፡-ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ይሓ ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር

✨ messages.ai_summary
Yiha Real Estate invites bids for the open auction sale of various used items, including electrical goods, plumbing, lift and generator parts, office supplies, mechanical items, doors, chairs, aluminum materials, and vehicle parts. Bidders may offer prices per item or in lots.
Save Tender