በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ ሊያሰራ ላቀደው አይሶሌሽን ክፍል ግንባታ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ ሊያሰራ ላቀደው አይሶሌሽን ክፍል ግንባታ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስከር ወረቀት ያላቸው፤ የ2018 ዓ.ም ንግድ ፈቃድ ያሳደሱ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ አስተዳደር ህንፃ 4ተኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ድረስ በመምጣት ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር በመክፍል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነድ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሰም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሽያል ሰነድ ሦስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ እና ቴከኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የርPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ዓይነት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በለሚ ኩራ ክፍለ ማ አስተዳደር ህንፃ 6ተኛ ፎቅ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ምህንድስና ግዢ ቡድን በሚገኘው ጨረታ ሳጥን በ16ኛው (አስራ ስድስት) ቀን እስከ ቀን 7፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን ቴከኒካል ሰነድ Technical proposal / እና ፋይናንሻል ሰነድ /financial proposal / ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን ጠዋት 8:00 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት /technical proposal / በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ አስተዳደር ህንፃ 4ተኛ የግዥ ቡድን ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከዚህ ቀደም ምንም ዓይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ውል ያቋረጠ ተወዳድሮ ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND of BID SECURITY) (40,000 ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም /UNCONDITIONAL BANK GUARANTEE/ በሎሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ፋይናንስ አስተዳደር ፑል ጽ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤
- ጽ/ቤቱ ባወጣው የግንባታ ጨረታዎች ከአንድ ፕሮጀከት በላይ በጨረታ መሳተፍ አይችልም፡፡ በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፈርማ አለማድረግ ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል ፡፡
- ከትንሹ ግምት በታች እና የተጋነነ ዋጋ ያስገባ ተቋራጭ ብሬክዳውን (BREAKDOWN) ማስገባት እንደሚገደድ እናሳውቃለን፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በከፍለ ከተማው ዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን በአካል ማቅረብ መረዳት ይቻላል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ማሳሰቢያ፡- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም የበአል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
አድራሻ፡- ፊጋ መብራት ጋር በወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ አስተዳደር ህንፃ 4ተኛ ፎቅ የግዥ ቡድን ላይ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የወረዳ 08 አሞራው ጤና ጣቢያ
✨ messages.ai_summary
Construction of an isolation unit at Amorao Health Center, District 08. Bidders must be licensed, tax-compliant contractors with valid registration, VAT certificates, and renewed competency documents. Contractors with prior contract breaches are disqualified.
