Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
  • Address Addis Ababa Ethiopia, Phone: 0116-454147/0116-453598 /0118-694931
  • Website
  • Deadline17 Sep 2026, 3:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price500 /አምስት መቶ ብር/
  • opening dateበዚሁ ቀን ከ9፡30
  • Categories Other , Vehicle , Battery

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ባለ 15 መቀመጫ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ቻርጀር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 01/18

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ባለ 15 መቀመጫ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ቻርጀር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
  2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 10:30 የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው በአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 208 በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  3. የጨረታው ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን 200,000.00 ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 9፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ9፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከመገናኛ አያት 49 ወይም ጣፎ መንገድ ከሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ከርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት

✨ messages.ai_summary
The Ethiopian Institute of Competitiveness and Job Leadership seeks bids for the procurement of new 15-seat electric vehicles and electric car battery chargers via open tender. Eligible bidders must hold a renewed trade license, business registration, VAT certificate, tax registration, supplier registration, and submit required documents.
Save Tender