Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
  • Address አምቦ ከተማ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር- የድሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ህንፃ ላይ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112609777
  • Website
  • Deadline09 Sep 2026, 2:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር)
  • opening dateSep 09, 2026, 2:30 PM
  • Categories Other , Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale

በአምቦ ሪጅን ስር በተለያዩ ቦታዎች- አምቦ፤ ወሊሶ፣ ቱሉ ቦሎ፤ ሰደን ሶዶ፤ ባኮ፤ እና ጌዶ ተከማችተው የሚገኙ ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


ያለገሉ እቃዎች ሽያጭ ግልጽ ጨረታማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/ሪ/ግ/ጨ/001/2019

በአምቦ ሪጅን ስር በተለያዩ ቦታዎች- አምቦ፤ ወሊሶ፣ ቱሉ ቦሎ፤ ሰደን ሶዶ፤ ባኮ፤ እና ጌዶ ተከማችተው የሚገኙ ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

 

የእቃው ዓይነት

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

 

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

 

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

 

1

 

ተቀቅለው ያገለገሉ የእንጨት ምሶሶዎችን

 

ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት

 

ጳጉሜ 04 ቀን 2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት

 

ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺ ብር)

 

 

1.      ማንኛውም የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የትኛውም አካል እና ማንኛውም የንግድ ፍቃድ የሌለው ግለሰብ የጨረታ ሰነድ ገዝቶ የጨረታ ዋስትና በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

2.    ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር (1000254843017 EEU Ambo District Connection Fee) በሚለው ገቢ በማድረግ እና የከፈሉበትን የባንክ ስሊፕ ይዞ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

3.    አድራሻ፡- አምቦ ከተማ ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር-- የድሮ ሃዮሜ ኮሌጅ ሕንፃ ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14

4.    ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ከላይ በሠንጠረዡ ውስጥ በተገለፀው መሠረት ሆኖ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5.    ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር፡ ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/001/2019 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፣

6.    ጨረታው ከላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣

7.    ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-112-609777 መደወል ይችላሉ።

8.    ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- የእንጨት ምሶሶዎችን በተመለከተ ፈፅሞ ለማገዶነት (ለምግብ ማብሰያነት) እና ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የማያገለግሉ ሲሆን ለመግዛት የሚቀርቡ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ግዥውን ፈፅመው ከወሰዱ በኋላ በሰው፣ በእንሰሳት እና በተፈጥሮ (አካባቢ) ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ በኃላፊነት መልሰው በሥራ ላይ የሚያውሉ መሆንና በዚሁ አግባብም እንደሚጠቀሙ በደብዳቤ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Service Ambo Region offers used wooden poles for sale via open tender. Poles are stored in Ambo, Woliso, Tulu Bolo, Seden Sodo, Bako, and Gedo. Any individual or entity, with or without a business license, may participate. Buyers must confirm poles won't be used for cooking fuel or power lines and will be reused responsibly.
Save Tender