በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ፕሮግራም ላይ በ2017/18 የምርት ዘመን በአደጋ ስጋት ስራ አመራር ዘርፍ የተመረተ ስንዴ በቆሎ እና ገብስ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ፈቃድ ላላቸው አካላቶች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የሶዶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ለእንስሳት ዘርፍ አገልግሎት እና በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የከተማ ማዘጋጃ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገድ አገልግሎት የሚውል ሎት 1 የእንስሳት መድኃኒት፣ ሎት 2 ገረጋንቲ አቅርቦትና ሎደር ማሽን በሰዓት በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ፈቃድ ባላቸው አካላቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።