ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ በአዲስ አበባ ከተማ’ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና መ/ቤት ሕንፃ ላይ ለሚገኙ ሠራተኞቹ ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት የምሳ አገልግሎት ማቅረብ የሚችል ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታ በማወዳደር አሸናፊ ከሆነው ጋር ውል በመፈፀም አገልግሎቱን ለመስጠት ይፈልጋል፡፡
ሕብረት ኢንሹራንስ አ.ማ. በተለያየ ወቅት የሚያካሂዳቸውን ዓመታዊ መደበኛ፤ እንዲሁም ሌሎች ያልታቀዱ ድንገተኛ ሁነቶችን በፎቶ እና በቪድዮ በከፍተኛ ጥራት በመቅረጽና ኤዲት በማድረግ የሚያስረክበው ድርጅት አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ለአንድ ዓመት የሚቆይ ውል (ኮንትራት) መፈራረም ይፈልጋል፡፡