Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Seed Enterprise (የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ)
  • Address ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ሕንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-416 03 09
  • Websitehttps://oromiaseedenterprise.com/
  • Deadline11 Sep 2026, 11:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 200.00 (ሁለት መቶ)
  • opening dateጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በዕለቱ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት
  • Categories Safety And Security , Ict Equipment'S And Its Accessories , Cctv Camera

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት ዓመት፡- CCTV CAMERA በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OSE/NCB/002/2019

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ለ2019 በጀት ዓመት፡- CCTV CAMERA በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡-

1.      የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣

2.    የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት፣

3.    የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No)፣

4.    የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸውጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

5.    ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፡- ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ ሰነድ ሶፍት ኮፒ (Soft copy) መግዣ ዋጋ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ 2፡30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።

የጨረታ ሳጥኑ በዕለቱ ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ሕንፃ /Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።

ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፤ ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-11፡30 ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 011-416 0309/ 011-466-2527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ

✨ messages.ai_summary
Oromia Seed Enterprise seeks bidders for CCTV cameras via open tender. Bidders must hold a valid trade license, VAT registration, TIN, and tax clearance proof. Tender documents are available for purchase; bids must be submitted in sealed envelopes by the specified deadline.
Save Tender