ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አራት ክፍለ ከተሞች ስር በሚገኙ አስራ ሁለት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ ፔስታሎዚ የህፃናት መርጃ ድርጅት /PCF/ ከተባለ አጋር ድርጅት ጋር በመሆን “ጥራት ያለው አካታች እና ፍትሐዊ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽነትን ማሻሻል” የሚል ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም በነዚህ አጋር ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ የሚከተሉት ክበባት የሚሆኑ የተለያዩ ግብዓቶችን በመግዛት ክበባቱን በማጠናከር የተማሪዎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ክበባቱም ፡-
- የሚኒ ሚዲያ ክበብ (Mini Media Club)
- የአካባቢ ጥበቃ ክበብ (Environmental Protection Club)
- የስርዓተ ፆታ ክበብ (Gender Club)
- የስፓርት ክበብ (Sport Club)
- የተማሪዎች መማክርት ክበብ (Student Council) ናቸው
በመሆኑም በዘርፉ የተሰማራችሁ እና ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፤ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም፡
- በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ቲን ነምበር ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የቫት/ቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እንዲሁም
- ቁሳቁሶቹን በተቀመጠው ስፔሲፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ የእቃዎቹን ጥራት ሳምፕል አቅርበው ማሳየት የሚችሉ እና ለእቃዎቹ ጥራት ዋስትና መስጠት የሚችሉ፤
- ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፓርት አጓጉዘው ድርጅቱ ወደሚያዘጋጀው ስቶር ማድረስ የሚችሉ፤
- በ Ethiopian Center for Development /ECD/ ስም የተዘጋጀ የ15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር/ የማስያዣ ዋስትና (CPO) ማቅረብ የሚችሉ፤
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት እለት አንስቶ ለ 7 (ሰባት) ተከታታይ የስራ ቀናት ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/ ቢሮ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ በነፃ በመውሰድ ቁሳቁሶቹን የምታቀርቡበትን ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ገቢ አድርጋችሁ እንድትወዳደሩ እንገልፃለን።
አድራሻ፡- ቦሌ አለም ህንፃ 7ኛ ፎቅ
ስልክ፡- 011 663 95 16/17
አዲስ አበባ
ማሳሰቢያ ፡- ድርጅታችን ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ኢትዮጵያን ሴንተር ፎር ዴቬሎፕመንት /ECD/