የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ እና የገቢ ማስገኛ ተቋማት የ2015 እና 2016 በጀት ዓመት የተሰሩ የሂሳብ እና የሰው ሀይል ስምሪት ስራዎችን በውጭ የኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል ፡፡
የአገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/ እና የገቢ ማስገኛ ተቋማት የ2015 እና 2016 በጀት ዓመት የተሰሩ የሂሳብ እና የሰው ሀይል ስምሪት ስራዎችን በውጭ የኦዲት ማስመርመር ይፈልጋል ፡፡
በመሆኑም በአገር ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- በዘመኑ የታደሠ ፈቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥ መጠኑ ብር 200,000 00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግ/ፋ አስ/ር ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 2- ማግኘት ይቻላል
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከ7/2/2017 ዓ.ም እስከ 27/2/2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዛት ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢሮ ቁጥር -2-- በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ28/02/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 2 በ28/2/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0335400837 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የዋግ ልማት ማህበር /ዋልማ/
