Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የቀጠሮ ማረፊያ ቤት ማዕከል ቀ/ማረ/ቤት አስተዳደር/
  • Address ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አጠገብ ፡ አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-71-63-33
  • Website
  • Deadline28 Nov 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Electrical And Electromechanical

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል በምድብ (ሎት አንድ) ልዩ ልዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ቂሊንጦ ለስራ አገልግሎት የሚውል በምድብ (ሎት ንድ) ልዩ ልዩ የጥገና እቃዎችን ናስትሮ፣ ባለ 2.5 ኤሌክትሪክ ገመድ፣ ባለ 4 ኤሌክትሪክ ገመድ፣ ባለ 36 ዋት ፍሎረሰንት አምፖል፣ ባለ 36 ዋት ሆልደር፣ ባለ 18 ዋት ሆልደር፣ ባለ 18 ዋት አምፖል፣ ሪዚስታንት ባለ 09 ሪዚስታንት ባለ 08 ብሬከር ባለ 25 ኢንች፣ ፖውዛ አንፖል 1500 ዋት፣ ፖውዛ ባለ 200 ዋት ሲልድ፣ የእጅ ጓንት፣ ድጂታል ቴስት ላይት፣ ቡርሽ 14×14 እርሎ ቡርሽ/ ተመሳሳይ፣ ሜትር ባለ 75 ሲባጎ ገመድ ባለ 4 ቲክነስ፣ ቶርኖ ማጠፊያ ትልቁ፣ የመበየጃ ፒንሳ፣ የበያጅ መነፅር፣ ማስከሪያ፣ ኤሌትሮድ ፐርማነንት 2.5 ሚስማር ባለ 4 ቁጥር፣ ሚስማር ባለ 9 ቁጥር፣ ሚስማር ባለ 10 ቁጥር፣ ሚስማር ባለ 12 ቁጥር፣ የቆርቆሮ ሚስማር አጭሯ፣ የድግን መጋዝ ምላጭ መቶ አለቃ፣ ታፕ የብረት ½   ታጥ የብረት ¾   ሬዲውሰር የብረት ¾ - ½   ሩቪነቶ ጎማኒ፣ የብረት ሶኬት ½ የብረት ሶኬት ¾ የብረት ኤልቦ ½ ኒብልስ የብረት ½ ኒብልስ የብረት ¾ ምጣድ ባለ 58 ስፋት፣ ጄሶ፣ የምጣድ ሶኬት፣ ተንጠልጣይ፣ ኮኔተር 150 AM ማብሪያ ማጥፊያ፣ ተንጠልጣይ ሬቬኔቶ ½ ሬቬኔቶ ¾ ጌት ቫልቭ ½   ጌት ቫልቭ ¾   ፊሜል ኤልቦ ½ ፊሜል ኤልቦ ¾ ሜል አዳፕተር ½ ሜል አዳፕተር ¾ ፊሜል አዳፕተር ½ ፊሜል አዳፕተር ¾  እና በምድብ (ሎት ሁለት) የሲቪል ሰራተኞች አልባሳት፣ ካኪ ጋወን፣ ብትን ነጭ ጨርቅ፣ አጭር የሴት ቆዳ ጫማ፣ ቴትሮን ኮትና ቀሚስ፣ የፀጉር መሸፈኛ፣ የፀጉር መሸፈኛ ባለ ጨርቅ ማሰሪያ፣ ፖፕሊን የሸሚዝ ብትን ጨርቅ፣ የተሰፋ ካኪ ሽርጥ፣ ባለ አበባ ሙሉ ቀሚስ፣ ካኪ ግልድም፣ ከጥጥ የተሰራ የውስጥ ልብስ፣ ዴስት ማስ የላስቲክ ጓንት፣ የላስቲክ ቦቲ ጫማ፣ ቴትሮን፣ የጋወን ብትን ነጭ ጨርቅ ባለ 6ሽ፣ ዶክተር ሹዝ፣ ቴትሮን ቱታ፣ ቡትስ ቆዳ ጫማ፣ የተሰፋ ሸሚዝ፣ ቴትሮን የጋውን ብትን ጨርቅ ብሉ ብላከ፣ አጭር የወንድ ጫማ፣ ሌዘር ጓንት፣ የመስክ ቆብ፣ ካኪ የተሰፋ ሸሚዝ፣ ኮትና ሱሪ፣ የዝናብ ልብስ፣ እስፖርት ቱታ፣ እስፖርት ቶርሽን ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡
  2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
  3. የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው
  4. የመንግስት /ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ፣ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፤ እንዲሁም በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከገቢዎች ጉምሩክ ባለስልጣን የዘመኑን ግብር ከፍለው ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆነ በጨረታው ለመሳተፍ ካደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፤
  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000007971347 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ክፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች ቴከኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል ሰነዶችን/ በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦሪጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትክክል በመፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴኒክ ሰነዶች ከኦሪጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ህዳር 19 ቀን 2017 . ከቀኑ 430 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ እንዲሁም የባንክ ዋስ የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፡፡
  11. ጨረታው ህዳር 19 ቀን 2017 . ከቀኑ 500 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  12. የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል፡፡
  13. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፤ እንዲሁም ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  14. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የዓመት በዓላት ከሆነና በተለያዩ ምክንያት ዝግ ከሆነ ጨረታው በሁለተኛው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- ቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር / ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጠገብ

ለበለጠ መረጃ:- 011-4-71-63-33/011-8-88-60-89/011-4-34-89-86

ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር

Save Tender