የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል:: ድርጅቱ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ያገለገሉ እቃዎች ለመሸጥ በድጋሚ
የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት (CCRDA) ከ50 ዓመታት በላይ በልማትና የበጎ አድራጎት ሥራ ላይ በማገልገል ላይ ይገኛል:: ድርጅቱ የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: እቃዎቹና የጨረታ ሰነዱ የሚገኙት ሃያ ሁለት የውሃ ልማት ቢሮ በስተጀርባ ጫካ ቡና አካባቢ በሚገኘው ትሪጎ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ IPHCE ቢሮ ነው:: ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናትና ሰዓት እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ ተመልክተው ለጨረታው ባወጣው መመሪያ መሠረት መወዳደር ይችላሉ::
ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በአንድ ሳምንት ውስጥ ተረክቦ ማንሳት አለበት::
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት እቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ማህበራት ህብረት
አድራሻ :- ቃሊቲ ከአሽከርካሪዎችና መካኒኮች ማሰልጠኛ ማዕከል
ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር ፡- 0114-390322 ወይም 0114-393393
