ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
ዘመን ባንክ አ.ማ ያገለገሉ ንብረቶች እና ሌሎች ዕቃዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
(በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ)
ዘመን ባንክ አ.ማ. ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን (የቢሮ ፈርኒቸሮችን) ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
የጨረታ ደንቦች፡-
1. ንብረቶቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ተጫራቾች ከሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ሞተር ሳይክሎቹን “ጎፋ መብራት ኃይል ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ት/ቤት” አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ መመልከት ይችላሉ፤ ወይም በስልክ ቁጥር 0115-57-58-25/011 668 78 09 በመደወል ወይም ሰንጋ ተራ አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት 12ኛ ፎቅ ላይ በንብረት እና ሎጂስቲክ አስተዳደር መምሪያ በአካል በመቅረብ መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፣
2. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዋጋ መሙያ ቅጽ ከባንኩ የንብረት አሰተዳደርና ሎጂስቲክሰ መምሪያ በመግዛትና እና በመሙላት በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሰዉን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
3. ተጫራቾች በምድብ (ሎት) ተለይተዉ ከተቀመጡት ንብረቶች የመረጡትን ምድብ (ወይም ሁሉንም) ለመግዛት የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከቀነ- 11፡00 ድረስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 12ኛ ፎቅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
4. ጨረታው ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ ሐምሌ 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 03፡30 ሰዓት በባንኩ ህንጻ 19ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::
5. ጨረታው በሚካሄድበት ዕለትና ሰዓት መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው::
6. አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ለባንኩ ክፍያ መፈጸም አለበት:: ይህን ባያደርግ ግን ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
7. ንብረቶቹን ከማስተካከል፤ ከመጫንና ከማጓጓዝ ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።
8. ተጨማሪ የጨረታ ደንቦች የጨረታ ሰነድና የዋጋ መሙያው ቅጽ ላይ ተቀምጠዋል::
9. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ዘመን ባንክ አ.ማ
Sengatera, Ras. Abebe Aregay Street, P.O.Box 1212 Addis Ababa, Ethiopia
