መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 109
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ቁሳቁሶቹም:
- በእንጨት የተሠሩ መቃኖችና በሮች፣ ጠረጴዛና የጠረጴዛ ቶፖች ጣውላዎች፣ ሎከሮች፣ ልዩ ልዩ የወላለቁ የዴስክና የኮሜዲኖ ዕቃዎች:
- ያገለገለ ዊልቼሮች የተለያየ መጠን ዓይነት ያላቸው ያገለገሉ ወንበሮች፣ አሮጌ ሶፋዎች፤
- የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችና የአሌክትሪከ ኬብሎች፣ (ዴስክ ቶፕ፣ ዩፒ ኤስ፣ ፕሪንተሮች፣ የተለያዩ ያገለገሉ ፍሪጆች፣
- ፍሎረሰንት፣ ታንከሮችና ሌሎች ፋይበር ግላሶች፣ ካስኮች (የሴቶች ፀጉር መሥሪያ)፣ የአትክልት ማብቀያ ኮንቴይነሮች፣ ፋይሊንግ ካቢኔቶች፣ ተገጣጣሚ የመሬት ምንጣፍ፣ ብረት ድስቶችና ጎላዎች፤ የተቆራረጠ የቤት ክዳን ቆርቆሮ፤
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከፀበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ በቁጥር 1 እና 4 ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ብቻ) ከያዘ ሲፒኦ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ15ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን ዕሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0930-79-64-13 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
