በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በተለያዩ ምድቦች የተገለፁ የሴፍቲ እና ኖርማል ጫማዎች ሳሙና ሶፍት ቲሸርት እና ፎጣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ በተለያዩ ምድቦች የተገለፁ የሴፍቲ እና ኖርማል ጫማዎች ሳሙና ሶፍት ቲሸርት እና ፎጣ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ፡-
-
- በኢንዱስትሪው ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በመምጣት ዝርዝር መረጃ፤ የተጫራቾችን መመሪያ እና የዕቃዎችን ዓይነትና መጠን የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይችላሉ።
- በዋጋ ማቅረቢያ ላይ ተጫራቹ የዕቃው ዋጋ በሚለው አምድ ስር የሚሸጡበትን የነጠላ ዋጋ በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልፀው በታሸገ ኤቨሎፕ የኢንዱስትሪው - ሰፕላይ ቼን ማኔጅመንት ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
- ተጫራቾች የዕቃዎችን የተናጥል ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ትክክለኛ የተጫራች ስምና አድራሻ በታሸገው ኤቨሎፕ እና በመጫረቻ ሰነድ ላይ መገለፅ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የእቃዎችን ለተቀመጠው የነጠላ ዋጋ ድምር የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠው ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጪ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንዱስትሪው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የጨረታውን ውጤት በኢንዱስትሪው ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣ ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥራችን 0116670485/0118592286 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱ ላይ በየገጹ - ስምና ፊርማ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የቫት ሠርተፍኬት የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ኢንዱስትሪው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
አድራሻችን ፡- በመገናኛ ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከአምቼ ዝቅ ብሎ ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት
ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የኢትዮጵያ ፕላስቲክ ኢንዱስትሪ
አዲስ አበባ
