Tender Detail

Tender Details

  • Company የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ
  • Address ጋምቤላ : ኢትዮጵያ, Phone: 0948107127
  • Website
  • Deadline30 Nov 2024, 3:30 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Printing And Publishing

የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፋይናንስ ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት መደበኛ የበጀት መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አገልግሎት ላይ የሚውል ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የፋይናንስ ቢሮ 2017 በጀት ዓመት መደበኛ የበጀት መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ለማድረግ አገልግሎት ላይ የሚውል ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፤

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
  4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  5. የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፣
  6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትና ሌሎች ጠቃሚ ናቸው የሚሏቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ግዥ፣ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን የቢሮ ቁጥር 31 ቀርበው የማይመለስ ብር 300.00 ከፍለው መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የገንዘብ መጠን ወይም ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /../ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪውን ስም፣ አድራሻ የሚመለከት /ህጋዊ/ ወኪል የተፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን አረጋግጠው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ጨረታው ይህ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የካላንደር ቀናት አየር ላይ ይቆያል፡፡ የጨረታው ሣጥን 11ኛው ቀን ከቀኑ 930 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 1000 ሰዓት ላይ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ የግዥ ንብረትና ፋይናንስ አስተዳደር ቡድን የቢሮ ቁጥር 31 ይከፈታል፡፡ 10ኛው እና 11ኛው ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በአላት ቀን ላይ ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 930 ሰዓት ተዘግቶ ከላይ በተባለው ሰዓት ይከፈታል፡፡
  11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0948107127 ወይም 0933800793 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፋይናንስ ቢሮ

Save Tender