በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የአቀስታ ፖሊ/ቴ/ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም ለስልጠና አገልግሎት የሚውል የህንፃ ቁሳቁስ እቃዎች የኤሌከትሮኒክስ ፡ የፅህፈትና ቋሚ የቢሮ ዕቃ ፣ የጋርመንትና የደንብ ልብስ ፡ የግብርና ማሰልጠኛ፡ የፅዳት የአውቶ ማሰልጠኛ ዕቃ እና የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የአቀስታ ፖሊ/ቴ/ ኮሌጅ ለ2017 ዓ.ም ለስልጠና አገልግሎት የሚውል የህንፃ ቁሳቁስ እቃዎች የኤሌከትሮኒክስ ፡ የፅህፈትና ቋሚ የቢሮ ዕቃ ፣ የጋርመንትና የደንብ ልብስ ፡ የግብርና ማሰልጠኛ፡ የፅዳት የአውቶ ማሰልጠኛ ዕቃ እና የስፖርት ትጥቅ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑን የታደሰ በተጠቀሱት የንግድ ዘርፎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የሚሞሉት ዋጋ 200000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥ ተሳትፎ ያሸነፈውን እቃ ሳያቀርብ ቀርቶ በጨረታ እንዳይሳተፍ ደብዳቤ ያልተፃፈበት
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ እና ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለጨረታ ሲቀርቡ ኦርጅናል መረጃውን ቢያቀርቡ የተሻለ ይሆናል ፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ ::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒአ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም የራሱ ፊርማ መቀመጥ አለበት፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ እና በፖስታው ላይ የተሟላ አድራሻቸውን መጻፍና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ በግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 9 ከ16/3/2017 ዓ.ም እስከ 30/3/2017 ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ሲቻል ከዚያ በኋላ ኮሌጁ አያስተናግድም፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ በራሱ እስፔስፊኬሽን የሞላ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ፖስታውን ማስገባት ሲኖርበት ኦርጅናልና በአንድ ወይም አንድወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቂ በታሸገ ፖስታ በማሸግ በአቀስታ ፖሊ/ቴ/ኮሌጅ በግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከ30/3/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨርታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ፋይናስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 በ1/04/2017 ዓ.ም በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የVAT ወይም ቲኦቲ ተመዝጋቢዎች VATና ቲኦቲ ጨምራችሁ መሙላት አለባችሁ ይህን ጨምሮ ያልተሞላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 9 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0927377402 ወይም ስልክ ቁጥር 0917185277 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን በለጋምቦ ወረዳ የአቀስታ ፖሊ/ቴ/ ኮሌጅ
