በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የሚያዚያ 23 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት አንደኛ ዙር የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የሚያዚያ 23 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በ2019 በጀት አመት አንደኛ ዙር የሚከተሉትን እቃዎች በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 1 ደንብ ልብስ
ሎት 2 አላቂ የትምህርት እቃዎች
ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
ሎት 4 ቋሚ እቃዎች
ሎት 5 የህክምና መሳሪያዎችና መድሃኒቶች
በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በቅድሚያ መሟላት ይጠበቅባችኋል።
1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና የቫ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማከበሪያ ብር 4000 /አራት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታ ውጤት እንደታወቀ አሸናፊ ድርጅት ላሸነፈበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 በመክፈል ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
6. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ቀን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
7. ጨረታው የሚከፈተው አስረኛው ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ባለው የስራ ቀን 2፡30 ይሆናል።
8. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃ አይነት ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡- አድራሻች ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደ 41 እየሱስ መሄጃ አስፓልት ሲመጡ ከጤና ጣቢያው 100 ሜትር ከፍ ብሎ
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 01 11 54 90 55 ወይም 09 38 01 07 10 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 የሚያዚያ 23 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
