በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግልፅ ጨረታ ለሱቅ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል የተጫራቾች መመሪያ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ቁጥር 01
በራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል በግልፅ ጨረታ ለሱቅ አገልግሎት የሚውሉ ቤቶችን አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል የተጫራቾች መመሪያ በዚሁ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚሰማሩበት የስራ መስክ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ሱቆቹን ከአልኮል መጠጥ እና ጫት ንግድ እንዲሁም ቁማር ንግዶች አገልግሎት ላይ መዋል አይቻልም።
- አንድ ሰው ከአንድ ሱቅ በላይ መጫረት አይችልም ተጫርቶ የተገኘ ሙሉ ለሙሉ ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር ማንነታቸው የሚገልፅ ትክክለኛነቱ የተረጋገጠ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ስም የተሰራ ሲፒኦ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ከጨረታ ፖስታ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ከላይ የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ ፋ/ግ/ን/አስ/ ቢሮ ቁጥር 2 ቀርበው 200.00 ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው ሰነዱን በመውሰድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን መሙላትና በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልተው ለሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በአስረኛው የስራ ቀን 8፡00 ላይ ታሽጎ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በራስ ኃይሉ የስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል 1ኛ ፎቅ ላይ በግልጽ ይከፈታል።
- ከተባለው ቀን እና ሰዓት በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የተጫራቹ ወይም የህጋዊ ወኪሉ ስምና ፊርማ ያለበት መሆን አለበት።
አድራሻ ፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አጠገብ ወይንም መድኃኒዓለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ትልቁ አደባባይ ግሩም ሆስፒታል በሚወስደው 100 ሜትር በስተ ግራ ገባ ብሎ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ የራስ ኃይሉ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
አዲስ አበባ
