በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የቡራዩ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማከራየት ይፈልጋል።
የቄራ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የቡራዩ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ቄራ ለማከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የሚያሟሉ ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በስንቄ ባንከ በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1065422441218 የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ) ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ከቡራዩ ከፍለ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት በማስቆረጥ ከቡራዩ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ በስማቸው ያላቸውና የዘመኑን ግብርየከፈሉ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በፌዴራል ገ/ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገ/ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የቫት (የተጨማሪ እሴት ታክስ) ተመዝጋቢና የምዝገባ ምስከር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና በዘርፉ ከከልሉ የእንስሳት ጤና ኤጀንሲ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአገልግሎት ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ) በባንከ በተመሰከረለት (CPO) ከጨረታው ሠነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. በስሙ የተመዘገበ ከ7 ቫን የሥጋ መኪናዎች ሊብሬ በተወዳዳሪው ስም ያለው ማቅረብ የሚችልና ወይም ከዚያ በላይ ያለው እና በሥጋ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታው ሰነድ በግልጽ ቴከኒክ እና ፋይናሽያል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ ታሽጎ በፖስታው ላይ ተጽፎ ለየብቻው ታሽጎ የተከራዩ ስም ተጽፎበት ማቅረብ ይኖርበታል።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ የሥራ ቀን እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሠዓት አድራሻ በቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 107 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
6. ጨረታው በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡራዩ ከፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 ውስጥ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ለመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% Performance Bonad በማስያዝ በመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል።
ማሳሰቢያ፡-
ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከመደበኛ የሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
አሠሪው መ/ቤት የተሻለ መንገድ ከአገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከተፈለገ በስልክ ቁጥር (011-2604836) ወይም (011-2604879) ደውለው መረዳት ይችላሉ።
በሸገር ከተማ አስተዳደር የቡራዩ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
