Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline01 Sep 2026, 1:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price 500 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብሄራዊ ቲያትር አካባቢ በቤት ቁጥር 287/14 የሚገኘው ልዩ ስሙ አፊሶል ህንጻ ላይ ምድር ወለል 74.30ካሬ፣መዳረሻ (አንደኛ ፎቅ) 74.00 ካሬ እና ከምድር በታች 86.23 ካሬ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ሁለገብ ቢሮ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡


                                                           የቤት ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

                                                           ጨረታ ቁ.ፋሀኣዳ/ግዳ/026/2018

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ብሄራዊ ቲያትር አካባቢ በቤት ቁጥር 287/14 የሚገኘው ልዩ ስሙ አፊሶል ህንጻ ላይ ምድር ወለል 74.30ካሬ፣መዳረሻ (አንደኛ ፎቅ) 74.00 ካሬ እና ከምድር በታች 86.23 ካሬ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ሁለገብ ቢሮ በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1. ድርጅታችን ለኪራይ ያቀረባቸውን ከፍሎች በጨረታ መወዳደር/ መሣተፍ የሚፈልግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ከሰዓት በኋላ ከ7፡ 30 እስከ 9፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ıኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ከፍል በኢትዮጵያ መድን ድርጅት (Ethiopian Insurance Corporation) ስም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ (C.P.O) ወይም ለዘጠና ቀናት በሚቆይ ቅድመ ሁኔታን ባላስቀመጠ የባንከ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለገሐር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ማለትም ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም በድርጅቱ ዋናው መ/ቤት ግዥ ዳይሬከቶሬት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በ8፡ 30 ይከፈታል፡፡

5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

6. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር 011-5512400 የውስጥ መስመር 237/262 ወይም በቀጥታ 011-5504931 መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

                                                                         የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

 

 

✨ messages.ai_summary
Ethiopian Insurance Corporation seeks bids to lease a multi-purpose office in the Afisol Building, National Theatre area, House No. 287/14, with ground floor (74.30 sqm), first floor (74.00 sqm), and basement (86.23 sqm). Bidders must purchase tender documents and provide a bid security.
Save Tender