ካዮ አ/ፍ/ግ/ህ/ሥ/ዩ/ኃ/የተ በደ/ኢ/ክ/መንግስት የጌድኦ ዞን ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር አ/አደሮች በያዝነው ምርት ዘመን 2017 ዓ.ም ከዲላ ከተማ ከሚገኝ መጋዘን ወደ ማራገፍያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ የጨረታ ቁጥር 001/17
ካዮ አ/ፍ/ግ/ህ/ሥ/ዩ/ኃ/የተ በደ/ኢ/ክ/መንግስት የጌድኦ ዞን ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር አ/አደሮች በያዝነው ምርት ዘመን 2017 ዓ.ም ከዲላ ከተማ ከሚገኝ መጋዘን ወደ ማራገፍያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፍያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ መሠረት ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የመዳረሻ ዋጋ በጠጠር እና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ፣ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሰረት
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት፡፡
- ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጭ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብ እና መወዳደር አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ተጫራች ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን የጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስዛል፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 50 (ሃምሳ) ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና አይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከካዮ አ/ፍ/ግ/ህ/ሥ/ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ዲላ ከተማ ጪጩ ታክስ በታች በኩል ጌደኦ ዞን ሕብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ ይገኛል፡፡
ስልክ ቁጥር 0916189564/0463312660
ካዮ አትክልትና ፍራፍሬ ግ/ህ/ሥ/ዩ/ኃ/የተ
