Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidaama Broadcasting Corporation (የሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን)
  • Address ሀዋሳ ወንዶ ንግድ ኩባንያ ህንጻ ጀርባ በሚገኘው በኮርፖሬሽኑ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916037261
  • Website
  • Deadline19 Dec 2024, 10:30 AM
  • magazine
  • Bid Document Price
  • opening date
  • Categories Electrical And Electromechanical

ሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን በሐዋሳ ከተማ ባስገነባነው ህንጻ ፓሰንጀር ሊፍት G-6 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገጠም /ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

ሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን በሐዋሳ ከተማ ባስገነባነው ህንጻ ፓሰንጀር ሊፍት G-6 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገጠም /ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም  በዚህ  ጨረታ  መወዳደር  የሚችሉ

  1. ተጫራቾቹ በሊፍት ገጠማና አቅሪቢነት ፍቃድ ያላቸው
  2. በአጠቃላይ ሊፍት ሥራ መስከ የታደሰ የግንባታ ፍቃድ ሴርቲፊኬት ያላቸው
  3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  4. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው
  5. የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀን የማይመለስ ብር 500 እየከፈላችሁ ሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን ሀዋሳ አሮጌ መናኃሪያ ሌዊ ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ሲዳማ ቡና ህንጻ 3 ፎቅ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ለጨረታ ከሚያቀርቡት ዋጋ 1.5% ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO በሲዳማ ብሮድካስትንግ ኮርፖሬሽን ስም ተሰርቶ ከኦርጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛልና ፋይናሻል ፕሮፖዛል ጋር ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
  7. በጨረታ ዶክመንት ላይ አስፈላጊ የሆነ ቴክኒካልና ሌሎች አስፈላጊ መረጃችን መሙላት አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ቴክኒካል ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እንዲሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና አንድ ኮፒ እያንዳንዳቸው ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በላዩ ላይ የድርጅቱ ስም አድራሻና ፊርማ በማሳረፍ በጥንቃቄ በማሸግ ማስገባት አለባቸው፡፡
  9. ተጫራቾች ሊፍቱ የሚገነባበት ሳይት በራሳቸው ወጪ መጥተው ማየት አለባቸው::
  10. ተጫራቾቹ የሊፍቱን ዕቃዎች ሙሉ ለሙሉ በራሳቸው በማቅረብ ማንኛውንም የሊፍቱ ሥራ በተቀመጠው ዝርዝር መሠረት ሥራውን በራሳቸው አጠናቀው ማስረከብ አለባቸው፡
  11. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ሥራ ቀና፡ በአየር ላይ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ከቀኑ 430 ሰዓት የጨረታ ሣጥን ታሽጎ 500 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ሲሆን በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  12. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልምሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ  መረጃ  በስልክ  ቁጥር  0916037261  ደውሎ  መጠየቅ  የሚቻል  መሆኑን  እንገልጻለን፡፡

 

ሲዳማ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን

Save Tender