የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የዕቃ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2017 ዓ/ም የበጀት ዘመን ለትምህርት ስልጠና የሚውሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ዕቃዎች የሚገዛላቸው የትምህርት ክፍሎች
1. ኮንስትራክሽን ዲ/ት 2. ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዲ/ት 3. አርባን ግርነር ዲ/ት
4. ብዩልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ዲ/ት 5. አግሮ ፕሮሰሲንግ ዲ/ት
6. ሳንተሪ ኢንስታሌሽን ዲ/ት 7. የእንጨት ሥራ ዲ/ት 8. ጋርመንት ዲ/ት
9. አኒማል ፕሮዳክሽን 10. የሥልጠና ጽ/መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች
11. የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ዲ/ት 12. ማኒፋክቸሪንግ ዲ/ት
13. ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲ/ት 14. አውቶ መካኒክስ ዲ/ት 15. ሮድ ኮንስትራክሽን ዲ/ት
16. ሆቴል ዲ/ት 17. ፕላፕንግ ዲፖርትመንት 18. ሞተር ሳይክሎች
በመሆኑም ከላይ ለተዘረዘሩ የሥልጠና ዘርፎች ለመወዳደር የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች አቅራቢዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታውን ተወዳድሮ /አቅራቢ ድርጅት የ2017 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።
- የገንዘብና ኢኮ/ል/ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚችሉና ቋሚ ዕቃዎችን ገዥው መ/ቤት በአካል ቀርቦ ለማየት ከፈለገ ለመተባበር ፍቃደኛ ሊሆኑ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ዋጋው ከቫት ውጭና ከነቫቱ በፊት ተብሎ በጥራት መሞላት ይኖርበታል። እንዲሁም ቫት ከተካተተበት ተካቶበታል ተብሎ እንዲሁም ያልተካተተ ከሆነ አልተካተተም ተብሎ ሊጻፍ ይገባዋል ይህ ሳይሆን ቢቀር ቫት እንደተካተተ አድርጎ መ/ቤቱ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የጠቅላላ ዋጋ 2% ብር 10,000.00 የጨረታ ማስከበሪያውን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት አለበት ፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ከፖሊ ኮሌጁ ጋር ውል ተዋውሎ የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርበታል፤ በተጨማሪ ያሽነፈበትን ዕቃ በ15 ቀናት ውስጥ ለኮሌጁ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡ ይህ ሳይሆን ቢቀር ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት 10% ገንዘብ በቀጥታ ለፖሊ ኮሌጁ ገቢ ሆኖ ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ከታህሳስ 03/04/2017 ዓ/ም እስከ ታህሳስ 17/04/2017 ድረስ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከኮሌጁ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 4 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በኮሌጁ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር GOV 1000019294718 በማስገባትና አድቫይስ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይጠበቅበታል።፡
- ተጫራቾች የሚቀርቡትን የመወዳደርያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ ማህተም አሳርፎበት በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ጨረታዉ ታህሳስ 18/04/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ከጠዋቱ 4.00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባለመገኘታቸዉ የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉለውም ::
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁጥር 0463312719 ወይም 0433613848 ይደውሉ ::
የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
